Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለእኔ የምታስበው

Lenie Yemetasebew

2001 · ትራክ 9 · 5:32 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አሻግሬ አያለሁ ያንተን መልካምነት

ከቶ አልገምትህም አሁን ባለሁበት

ታሪክ የምትለውጥ ሁሉንም የምትቀይር

እኔ የማመልክህ ድንቅነህ እግዚአብሔር

ለእኔ የምታስበው በጐና ያማረ ነው (፫x)

አመሰግንሃለሁ (፫x)

አመሰግንሃለሁ (፫x)

የተገለጠውን ነገር ጸራለህ

በላይ ተሰውረህ ድንቅን ታደርጋለህ

ተዐምራትህ ብዙ እጅግ የበዛ ነው

ጌታ አሰራርህ ከሁሉም ልዩ ነው

ለእኔ የምታስበው በጐና ያማረ ነው (፫x)

አመሰግንሃለሁ (፫x)

አመሰግንሃለሁ (፫x)

ከሁኔታዎች በላይ ቃልህን አምናለሁ

ሚሰማኝን ሳይሆን የሩቁን አያለሁ

ከእንግዲህ ታምኜ በእምነት እኖራለሁ

የተናገርከኝንም እንዳገኝ አውቃለሁ (፪x)

ኃይልህ ብዙ ሳለ ጠላቶች ቢዋሹም

አንተ ግን አንተ ነህ ከቶ አትለወጥም

መልካምነትን በማድረግ ደስ ይለሃልና

አቤቱ የእኔ ጌታ ይሁን ለአንተ ምሥጋና

ለእኔ የምታስበው በጐና ያማረ ነው (፫x)

አመሰግንሃለሁ (፫x)

አመሰግንሃለሁ (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ