ምሥጋና ሲያንስህ ነው
Mesgana Siyanseh New
2001 · ትራክ 5 · 5:38 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ሲያንስህ ነው
ዝማሬ ሲያንስህ ነው
አምልኮ ሲያንስህ ነው
ውዳሴ ሲያንስህ ነው
ከአደረከው ጋራ ሳወዳድረው
ከሰራኸው ጋራ ሳመዛዝነው (፪x)
ከተደረገልኝ ነገር አንዱም አይገባኝም ነበር (፪x)
እንዲሁ በፀጋ ወደህ ከአደረከው
ጌታ ክበር እንጂ ሌላ ምን እላለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሠማያዊ ብርሃን በልቤ ውስጤ በርቷል
የጌታዬ ማዳን ነፍሴን አግኝቷታል
ከዘለዓለም ጥፋት ከፍርድ አምልጫለሁ
በትንሳኤው ጉልበት አዲስ ሰው ሆኛለሁ
ኢኸው ምሥጋናዬን ለአንተ አበዛለሁ
ኢኸው ዝማሬዬን ለአንተ አበዛለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ሲያንስህ ነው
ዝማሬ ሲያንስህ ነው
አምልኮ ሲያንስህ ነው
ውዳሴ ሲያንስህ ነው
ከአደረከው ጋራ ሳወዳድረው
ከሰራኸው ጋራ ሳመዛዝነው
ከተደረገልኝ ነገር አንዱም አይገባኝም ነበር (፪x)
እንዲሁ በፀጋ ወደህ ከአደረከው
ጌታ ክበር እንጂ ሌላ ምን እላለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ክቡር ኃያል ጌታ የእስራኤል ተዋጊ
በአለቀ ሰዓት ላይ የምስደርስ ታዳጊ
አዋጅን በአዋጅ በሥልጣንህ ሽረህ
በድል አራመድከኝ ታሪኬን ቀይረህ
ኢኸው ምሥጋናዬን ለአንተ አበዛለሁ
ኢኸው ዝማሬዬን ለአንተ አበዛለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ሲያንስህ ነው
ዝማሬ ሲያንስህ ነው
አምልኮ ሲያንስህ ነው
ውዳሴ ሲያንስህ ነው
ከአደረከው ጋራ ሳወዳድረው
ከሰራኸው ጋራ ሳመዛዝነው
ከተደረገልኝ ነገር አንዱም አይገባኝም ነበር (፪x)
እንዲሁ በፀጋ ወደህ ከአደረከው
ጌታ ክበር እንጂ ሌላ ምን እላለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፊትህ እቀርባለሁ በብዙ ምሥጋና
ጌታ ለውለታህ ምላሽ የለኝምና
የከንፈሬን ፍሬ እንካ ተቀበለው
ሕያው መስዕዋቴ ማደሪያህን ይሙላው
ኢኸው ምሥጋናዬን ለአንተ አበዛለሁ
ኢኸው ዝማሬዬን ለአንተ አበዛለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ