አመሰግንሃለሁ
Amesegenehalehu
2001 · ትራክ 10 · 4:31 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አመሰግንሃለሁ (፫x) ጌታ አመሰግንሃለሁ
ቁጥር 1 · Verse 1
አመሰግንሃለሁ (፫x) ጌታ አመሰግንሃለሁ
ነፍሴ አንተን ታከብርሃለች ሁልጊዜም ትባርክሃለች
መልካም ነህና ጌታ ለእኔ አመሰግንሃለሁ በዘመኔ
መልካም ነህና ኢየሱስ ለእኔ አመሰግንሃለሁ በዘመኔ
እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንዳሳቡም ለተጠሩት
ነገር ሁሉ ለበጐ ነው የሚደረገው የሚሆነው
እኔም አየሁ መልካምነትህን
ለሚታገሱ ቸር መሆንህን (፬x)
አዝማች · Chorus
አመሰግንሃለሁ (፫x) ጌታ አመሰግንሃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ነፍሴ አንተን ታከብርሃለች ሁልጊዜም ትባርክሃለች
መልካም ነህና ጌታ ለእኔ አመሰግንሃለሁ በዘመኔ
መልካም ነህና ኢየሱስ ለእኔ አመሰግንሃለሁ በዘመኔ
በጐነትህን ለመናገር ቸር መሆንህንም ለመመስከር
አንደበቴን እከፍታለሁ እግዚአብሔር መልካም ነህ እላለሁ
በምሥጋና ልዘምርልህ አዲስን ቅኔም ልቀኝልህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ