አሜን ይገባሃል
Amien Yegebahal
2001 · ትራክ 7 · 5:22 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የምሥጋናን መስዋዕት እሰዋለሁ
የከንፈሬን ፍሬ አቀርባለሁ
እግዚአብሔር ብቻህን አምላክ ነህና
ልትወደስ ይገባሃልና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ይገባሃል አሜን ይገባሃል (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
. (1) . በበገና
በአዲስ ዝማሬ በምሥጋና
እቀኝልሃለሁኝ በክብሬ
ዝማሬም ይፈልቃል ከከንፈሬ
አዝማች · Chorus
ክብር ለአንተ ሃሌሉያ ክብር ላንተ (፬x)
ይገባሃል አሜን ይገባሃል (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ያደረጋትን ድንቅ ልጸሙ
በአደባባዮቹ የምትቆሙ
እስኪ ተቀኙለት ለዚህ ጌታ
ከቅዱሳን ጋራ በደስታ
አዝማች · Chorus
ክብር ለአንተ ሃሌሉያ ክብር ላንተ (፬x)
ይገባሃል አሜን ይገባሃል (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ሠማያትን በስንዝር የለካህ
(ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን)
የምድርን መሰረት ያጸናህ
(ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን)
ባሕሩንና የብሱን የለየህ
(ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን)
የብርታትህን ጉልበት ያሳየኸን
(ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ ሆ ሃሌሉያ (፬x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ዙፋንህ ከጥንት ከዘለላለም
(ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን)
የእኛ ጌታ የሚመስለህ የለም
(ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን)
የሁሉ አዛዥ የሁሉ የበላይ
(ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን)
እግዚአብሔር ነህ ብቻህን ኤልሻዳይ
(ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ ሆ ሃሌሉያ (፬x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ሃሌሉያ ሆ ሃሌሉያ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ