ሃሌሉያ
Hallelujah
2001 · ትራክ 4 · 6:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ እውነት አለ
እግዚአብሔር አምልኮንና ምሥጋናን ይወዳል
ግዑዛን ፍጥረታት እንኳን ይህን ተረድተው
ቀንና ሌሊት ሳያቋርጡ ያመልኩታል
የእጆቹ ሥራ የሆንንና ፍቅሩን ያየን እኛማ
እንዴት...
ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች
ሌሊት ለሌሊቱ ቀትር ትናገራለች
ድምጻቸውን ከቶ ሳያሰሙ
ፍጥረት ሁሉ ለአንተ ሲያዜሙ
እኔም ልቤ በዚህ ተደነቀ
የምሥጋና ዜማ አፈለቀ
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ ሃሌሉያ
ሃሌ ሃሌሉያ (፬x)
(ሃሌሉያ) ሃሌ ሃሌሉያ
(ክብር ለአንተ ኢየሱስ) ሃሌ ሃሌሉያ
ሃሌ ሃሌሉያ (፪x)
(ሃሌሉያ)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዓይኖቼን ወደ ላይ አቀናለሁ
እጆቼን ወደ አንተ አነሳለሁ
በእውነት በመንፈስ አመልክሃለሁ
በእውነት በመንፈስ አመልክሃለሁ (፪x)
ሠማያት ክብርህን ያሳየሉ
እግዚአብሔር አለ እያሉ ይናገራሉ
ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ቢልም
የዓለም ምስክር እራስህን አልተውክም
የማይታየው ባሕሪህ ታይቷል
ለዘለዓለም ኃይልህም ተገልጧል
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) ሃሌሉያ
ፀሐይም . (1) . ታወጣለች
እስከ ምድር ዳርቻም ድረስ ታዞራታለህ
ከዋክብርትም በሌ'ት የምትመራ
የጨረቃን ብርሃን የምታበራ
ከአንተ በቀር ጌታ አምላክ ማነው
በህዋ ላይ ሙሉ ስልጣን ያለህ
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) ሃሌሉያ
ሃሌ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ)
ሃሌ ሃሌሉያ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኢየሱስ አንተ በሠማይና በምድር
መካከል ታላቅ አምላክ ነህ
እንደ አንተ ያለ የለም
በሠማይም የለም ፤ በምድርም የለም
ታላቅነት ገናናነት ፣ ክብር ፣ ምሥጋና ፣
ባለጠግነት ሁሉ ለሥምህ ይሁን
አሜን !
አዝማች · Chorus
ዓይኖቼን ወደ ላይ አቀናለሁ
እጆቼን ወደ አንተ አነሳለሁ
በእውነት በመንፈስ አመልክሃለሁ
በእውነት በመንፈስ አመልክሃለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ