Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዓለም አታላይ

Alem Atalay

2019 · ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዓለሙም ምኞቱም አንድ ላይ ጠፊ ነው (፪x)

ዘለዓለም የሚያኖር የጌታን ፍቃዱን ማድረግ ነው (፪x)

አትታለል ልቤ በሚያብለጨልጨው

ከክፋቱ/ከአመጹ ጋራ ይህ ዓለም ጠፊ ነው (፪x)

ዓለም ዓለም አታልይ ናት (፪x)

እውነት ሕይወትና መንገድ ጌታ ኦ ለታመኑበት (፪x)

ከእሳት ተጠብቆ ለሚቆየው ዓለም (፪x)

ነፍሴ አትጓጊለት በፍፁም ይቅርብሽ ግድየለም (፪x)

ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት እርሱ ብቻ

ከእሳት ከጨለማው በእምነት ማምለጫ (፪x)

ዓለም ዓለም አታልይ ናት (፪x)

እውነት ሕይወትና መንገድ ጌታ ኦ ለታመኑበት (፪x)

ሕይወትና ተስፋ የዘለዓለም ደስታ (፪x)

በእውነት ለታመኑበት የሚሰጥ ከጌታ (፪x)

ይህን ያስተዋለ ጌታን ሙጥኝ ይላል

ከዚህ ዓለም እድፈት እራሱን ያነጿል (፪x)

ዓለምን አትርፎ ሰው ነፍሱን ቢያጐድላት

ከቶ ምን ሊጠቅመው ሁሌ ላይኖርባት

ብልጭልጯን ንቆ እንደ ቃሉ የኖረ

እርሱ ነው ጠቢብ ሰው ያ ነው የተማረ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ