ከምንጩ
Kemenchu
2019 · ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከምንጩ ስለቀዳሁ ስለጠጣሁ ስለረካች ነፍሴ
ምህረት ስላገኘሁ አቀርባለሁ ክብርና ውዳሴ
በደሙ ስለዋጀኝ ስላዳነኝ የዘለዓለም አምላክ
ለኪዳኑ ስላሰበኝ ደስ ይለኛል ጌታዬን ስባርክ
ላመስግነው ከፍ ይበል መድህኔ
ስላዳነኝ ከሞት ከኩነኔ
ሥሙ ይክበር የጸዮኑ አለት
ተቆረጠ የኀጢአት ሰንሰለት
ቁጥር 1 · Verse 1
ለቤዛ ቀን በእርሱ ታትሜያለሁ
በመንፈሱ ልደት አግኝቻለሁ
ሠማያዊ ዜጋ የመንግሥቱ
ተመረጥኩኘ እንድኖር በእርስቱ
ፀጋ ሰጠኝ የዘለላእም ደህንነት
ታማኝ ጌታ ለተደገፉበት
ምሥጋናዬ ይኼው በየእለቱ
ላገልግለው በደስታ በቤቱ
አዝማች · Chorus
ከምንጩ ስለቀዳሁ ስለጠጣሁ ስለረካች ነፍሴ
ምህረት ስላገኘሁ አቀርባለሁ ክብርና ውዳሴ
በደሙ ስለዋጀኝ ስላዳነኝ የዘለዓለም አምላክ
ለኪዳኑ ስላሰበኝ ደስ ይለኛል ጌታዬን ስባርክ
ላመስግነው ከፍ ይበል መድህኔ
ስላዳነኝ ከሞት ከኩነኔ
ሥሙ ይክበር የጸዮኑ አለት
ተቆረጠ የኀጢአት ሰንሰለት
ቁጥር 2 · Verse 2
አምልኮዬ ለመድሃኒዓለም
ታላቅ ስሙ ይመስገን ዘለዓለም
ለሚገዛው ሠማይን ምድርን
አውጃለሁ ዘምራለሁ ክብሩን
ለታደገኝ ለታማኝ ወዳጄ
ዘምራለሁ በደስታ ፈቅጄ
አወራለሁ ፍቅሩን ተዐምራቱን
እርሱ ብቻ መድሃኒት መሆኑን
አይገርምም ወይ በአምላክ መታሰቤ
ላገለግል ለአመልከው ቀርቤ
የአዲስ ኪዳን አገልጋይ በቤቱ
ሎሌ አደረገኝ ጌታ በችሎቱ
ኢየሱስ ይክበር ይድመቅ በሕይወቴ
እርሱ አይደል ወይ ስሬ መሰረቴ
ጠጥቻለሁ የዘለዓለም ውሃ
ለመለመ የነፍሴ በረሃ
አዝማች · Chorus
ከምንጩ ስለቀዳሁ ስለጠጣሁ ስለረካች ነፍሴ
ምህረት ስላገኘሁ አቀርባለሁ ክብርና ውዳሴ
በደሙ ስለዋጀኝ ስላዳነኝ የዘለዓለም አምላክ
ለኪዳኑ ስላሰበኝ ደስ ይለኛል ጌታዬን ስባርክ
ላመስግነው ከፍ ይበል መድህኔ
ስላዳነኝ ከሞት ከኩነኔ
ሥሙ ይክበር የጸዮኑ አለት
ተቆረጠ የኀጢአት ሰንሰለት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ