Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የማይለዋወጥ

Yemayelewawet

2019 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ብቻ ነው

እግዚአብሔር ብቻ

ነገር እንደነበረ እንዳለ አይቀርም (፪x)

የማይለዋወጥ የማይቀያየር

ጸንቶ የሚኖረው

እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)

ዝና ክብር ቋሚ አይደለም

ሃብት አያኖር ለዘለዓለም

ዓለም መልኳ ተለዋጭ ነው

ያው የሆነው ክርስቶስ ነው

ሕይወት ኢየሱስ ነው

ነገር እንደነበረ እንዳለ አይቀርም (፪x)

የማይለዋወጥ የማይቀያየር

ጸንቶ የሚኖረው

እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)

ትላንት ዛሬም ለዘለዓለም

ያው የሆነው ቤዛ ለዓለም

ማይለወጥ ማያረጀው

ጌታ ብቻ የማይሞተው

ትንሳኤ ሕይወት ነው

ነገር እንደነበረ እንዳለ አይቀርም (፪x)

የማይለዋወጥ የማይቀያየር

ጸንቶ የሚኖረው

እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)

ፀሐይ ብርሃን ስትከለክል

ጨረቃዋም ደም ስትመስል

ዓለም አላት መጨረሻ

ያለ ሚኖር ጌታ ብቻ

የዘለዓለም አምባ

ነገር እንደነበረ እንዳለ አይቀርም (፪x)

የማይለዋወጥ የማይቀያየር

ጸንቶ የሚኖረው

እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)

"እግዚአብሔር ብቻ ነው

እግዚአብሔር ብቻ (፬x)"

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ