ለእኔ ክብሬ
Lenie Kebrie
2019 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ነው ለእኔ ክብሬ
ውበት ሞገስ ዘውድ አክሊሌ (፪x)
ከቶ የማይርቅ በፍፁም ከአጠገቤ
ሚራራልኝ ክብሬ ነው ጥጋቤ
አይጓደል በፍፁም ምሥጋናዉ
ሥሙ ይክበር ይድመቅ ዕልልታው
ቁጥር 1 · Verse 1
በቅዱሳን ጉባኤ ህብረት መሃል
ሊመሰገን ሊከብር ይገባዋል
መልካም መዓዛ ሆኖ ያርግ መሥዋዕቴ
ለወደደኝ አፍቃሪ መድሃኒቴ
ይድመቅ ጭብጨባው ይድመቅ ዕልልታውም ይሰማ
ምሥጋና በአሪያም ክብር ለእርሱ ነውና (፪x)
የአገኘሁት ደህንነት ለመንፈሴ
ዳግም ልደት በደሙ መቀደሴ
የአምላክ መንግሥት ወራሽ አድርጐኛል
ባመሰግን ብዘምር ያንስበታል
ሆ ትበል ዛሬ ነፍሴ
ታምጣ ለእርሱ ምሥጋና
ውዳሴ ለንጉሡ
ጌታ ድንቅ ነውና (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ነው ለእኔ ክብሬ
ውበት ሞገስ ዘውድ አክሊሌ (፪x)
ከቶ የማይርቅ በፍፁም ከአጠገቤ
ሚራራልኝ ክብሬ ነው ጥጋቤ
አይጓደል በፍፁም ምሥጋናዉ
ሥሙ ይክበር ይድመቅ ዕልልታው
ቁጥር 2 · Verse 2
ይዘምራል ጌታ ነው ክብሬ እያለ
በአምላኩ ሰው መሆኑን ያስተዋለ
ሕይወት የለውም ከጌታ ኢየሱስ ሌላ
የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የእርሱ ተድላ
ይድመቅ ጭብጨባው ይድመቅ ዕልልታውም ይሰማ
ምሥጋና በአሪያም ክብር ለእርሱ ነውና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ