በአምላኬ
Beamlakie
2019 · ትራክ 13 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በአምላኬ በስራው ከምደነቅ በቀር
ቁጥር 1 · Verse 1
በቂ ቃላት የለኝም ዘርዝሬ እንዳልናገር (፪x)
ሺህ ቃላት ደርድሬ በሺህ ቃላት ባወራው
የአምላኬ ቸርነት ከዚያም በላይ በላይ ነው
ዝም ብዬ ሁሌ አመሰግናለሁ
እርሱ በሰጠኝ ፀጋ መልሼ አከብረዋለሁ
ለአምላኬ ምሥጋናው ብዙ ነው
በደስታ ቆሜ ላመስግነው
የዕልልታው ድምጽ በቤቱ ይሰማ
ውዳሴ ለሆነው ገናና ክብርም ለእርሱ ነውና
ይደርደር በገናው ይድመቅ ዕልልታው ይሰማ
የጌታን ክብር ላወራ ቆሜያለሁ እኔማ
በጐነቱን እንድናገር አምላኬ መርጦኛል
ለእርሱ መለየቴን ሳስብ ምሥጋና ሞልቶኛል
ምህረቱ ከአእምሮ በላይ ነው
ይቅርታው ነው ወደር የሌለው
ያመልካል ብዙ የተተወለት
ይወዳል ምህረት የበዛለት
አምላክ ድንቅ ያደረገለት
ይሰበር ሽቶ ብልቃጡ መዓዛው ያወደው
ከእግሮቹ ስር ዝቅ ብዬ ጌታዬን ላምልከው
ግድ የለም ዙሪያ ገባዪ በእኔ ግር ቢለው
ምን ያህል እንደወደደኝ እኔ ነኝ የማውቀው
አዝማች · Chorus
በአምላኬ/በጌታዬ በስራው ከምደነቅ በቀር
ቁጥር 2 · Verse 2
በቂ ቃላት የለኝም ዘርዝሬ እንዳልናገር (፪x)
ሺህ ቃላት ደርድሬ በሺ ቃላት ባወራው
የአምላኬ ቸርነት ከዚያም በላይ በላይ ነው
ዝም ብዬ ሁሌ አመሰግናለሁ
እርሱ በሰጠኝ ፀጋ መልሼ አከብረዋለሁ
በፍቅሩ እጆቼን ይዞኛል
አይደክምም ሁሌ ይታገሰኛል
ኢየሱስ ኢየሱስ ልበለው
መድሃኒት ለነፍሴ ፈውስ ነው
ክብር ታማኝ ለሆነው
ይክበር የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ
ውዳሴ በሠማይ በምድር በታላቅ ዕልልታ
እስትንፋስ ያለው ይዘምር ይውጣ ምሥጋናዉ
በአባቱ ቀኝ በላይ ከብሮ ጌታ ለሆነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ