Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይገባሃልና

Yegebahalena

2019 · ትራክ 11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የጌታዎች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ

የይሁድ አንበሳ የናዝሬቱ ኢየሱስ

በአምባ ላይ ፈረስ የምትቀመጠው

በክብር በግርማ የምትመለሰው

የዘለዓለም ተስፋችን ኢየሱስ

የእግዚአብሔር ልጅ የደህንነታችን ራስ

ይገባሃልና (፫x) ኦሆ

ይገባሃልና (፫x) ኦሆ

ፊትህ እንደፀሐይ በሃይል ያበራል

ፍቅርህ ከዕንቁ ይልቅ ልብን ይማርካል

ውበትህ ያማረ ክብርህን ተላብሰሃል

ተመስገን ጌታችን ተባረክ ብለናል

በምድር ክብር በሠማይ

ይገባሃልና መንገሥ ከሁሉም በላይ

ይገባሃልና (፫x) ኦሆ

ይገባሃልና (፫x) ኦሆ

ብዙዎች ተገዙ ፍቅርህን ተረድተው

እንደ እግዚአብሔር ያላ ማንም የለም ብለው

ድምጻቸው ተሰማ ከየማዕዘኑ

ቅኔን ተቀኙልህ በስምህ የዳኑ

ተመስገን ተባረክ ብለው

ዘምረው አይጠግቡም ደስታህ ኃይላቸው ነው

ይገባሃልና (፫x) ኦሆ

ይገባሃልና (፫x) ኦሆ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ