ይገርመኛል
Yegermegnal
2019 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ይገርመኛል የአምላኬ ፍቅር ቸርነቱን
አልታክትም ሁሌ ባወራው ምህረቱን
እርሱ በሰራው ጸድቅ እኔን ያኖረኛል
ስለመዳኔ ላከብረው ይገባኛል ኦሆ
ላመስግነው ከፍ ላድርገው ክብርን ልስጠው ኦሆ
በሠማዩ መዝገብ ስሜን ስለጻፈው
ደስ ይለኛል ጸድቄአለሁኝ በእርሱ ስራ ኦሆ
እኖራለሁ ድንቁን ታሪኩን ሳወራ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢየሱስ መድኅኔ ማረፊያ ሆኖኛል
ከሞት ከጨለማ መንጥቆ አውጥቶኛል
የከበረ ስሙን ዘወትር እየጠራሁ ቅኔን እቀኛለሁ
በታላቅ ጉባኤ በልጆቹ መሃል አመሰግናለሁ
በልጆቹ መሃል አመሰግናለሁ (፫x) አመሰግናለሁ
ተመስገን ትላለች እርሱ ያዳናት ነፍሴ
ሳመልከው ደስ አለኝ በእውነት በመንፈሴ
አድናቆቴም ይኸው አክብሮቴም ይኸው ፊቱ ልስገድለት
ለጌቶቹ ጌታ ለነገሥታት ንጉሥ ሞገስ ይሁንለት
ለጌቶቹ ጌታ ሞገስ ይሁንለት ሞገስ ይሁንለት
ለነገሥታት ንጉሥ ለጌቶቹ ጌታ ሞገስ ይሁንለት
አዝማች · Chorus
ይገርመኛል የአምላኬ ፍቅር ቸርነቱን
አልታክትም ሁሌ ባወራው ምህረቱን
እርሱ በሰራው ጸድቅ እኔን ያኖረኛል
ስለመዳኔ ላከብረው ይገባኛል ኦሆ
ላመስግነው ከፍ ላድርገው ክብርን ልስጠው ኦሆ
በሠማዩ መዝገብ ስሜን ስለጻፈው
ደስ ይለኛል ጸድቄአለሁኝ በእርሱ ስራ ኦሆ
እኖራለሁ ድንቁን ታሪኩን ሳወራ
ቁጥር 2 · Verse 2
አምላክ አባት ሆነኝ በወንጌል አምኜ
በደሙ ዋጋ ገዛኝ እንድኖር ልጁ ሆኜ
እንግዲህ ምን ልበል ስለታላቅ ፍቅሩ ከቶ ምን ልናገር
ማለዳ ማለዳ መዳኔን እያሰብኩ ከማመስገን በቀር
ማለዳ ማለዳ መዳኔን እያሰብኩ ከማመስገን በቀር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ