Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልነካም

Alnekam

2009 · ትራክ 5 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ወጣለሁ ገባለሁ በልዩ ጥበቃ

ኢየሱሴን አልፎ ማነው እኔን ሚነካ

አልነካም አልነካም

በጠላቴ ላልነካ

ሸፍኖኛል የኢየሱስ ደም (፪x)

ከአቤል ደም ይልቅ የሚናገር ደሙ

እስከዛሬ ድረስ ትኩስ በመሆኑ

የወረወርው ቀስት ፈልጎ አጥቶኛል

የኢየሱሴ ደም በሙላት ጋርዶኛል

ኃይል አለውና የኢየሱሴ ደም (፪x)

ጋርዶኛልና የኢየሱሴ ደም (፪x)

ወጣለሁ ገባለሁ በልዩ ጥበቃ

ኢየሱሴን አልፎ ማነው እኔን ሚነካ

አልነካም አልነካም

በጠላቴ ላልነካ

ሸፍኖኛል የኢየሱስ ደም (፪x)

ክፉ እንዲደሰት እንዲስቅ በእኔ

ደግሶ እንዲበላ አይፈቅድም መድህኔ

የቀባውን ሊያድን ይወጣል በግርማ

አድኖኝ ስላየሁ እላለሁኝ ዘና

ኃይል አለውና የኢየሱሴ ደም (፪x)

ጋርዶኛልና የኢየሱሴ ደም (፪x)

ወጣለሁ ገባለሁ በልዩ ጥበቃ

ኢየሱሴን አልፎ ማነው እኔን ሚነካ

አልነካም አልነካም

በጠላቴ ላልነካ

ሸፍኖኛል የኢየሱስ ደም (፪x)

ምክር ተመክሮብኝ መልክተኞች መጡ

በክፉ ሴራቸው ህይወቴን ሊያጠምዱ

ሰፈሬ ሲደርሱ አልቻሉም ሊቀርቡኝ

በኢየሱሴ ደም ተሸፍኜ አዩኝ

ኃይል አለውና የኢየሱሴ ደም (፪x)

ጋርዶኛልና የኢየሱሴ ደም (፪x)

አልነካም አልነካም

በጠላቴ ላልነካ

ሸፍኖኛል የኢየሱስ ደም (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ