በእኔ ዘመን
Benie Zemen
2009 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንበጣ አይደለሁም ትንሽ ምናምንቴ
ፈቃድን አልሰጠውም እንዲስቅ ጠላቴ
በዘመኔ ላይ መልካም መልካሙን እናገራለሁ
የኢየሱስ ወንጌል በህይወቴ ላይ ሲሰራ አያለሁ
አዝማች · Chorus
በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አትደግ ብሎ ትላንት የረገመኝ
ጉድ ትሆናለህ ታያለህ እኮ ያለኝ
የርግማን ትንቢቱ ይፍረስ በጌታ ሥም
ልቤማ ደንግጦ ለርሱ እጅ አልሰጥም
አዝማች · Chorus
በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከዘር ማንዘሮቼ ተወራርሶ የመጣ
ነፃነት ከልክሎ መንገዴን የዘጋ
ዛሬ በየሱስ ስም ጉልበቱ ይመታ
ወዳጄ ብቻ ነው በቤቴ ላይ ጌታ
አንበጣ አይደለሁም ትንሽ ምናምንቴ
ፈቃድን አልሰጠውም እንዲስቅ ጠላቴ
በዘመኔ ላይ መልካም መልካሙን እናገራለሁ
የኢየሱስ ወንጌል በህይወቴ ላይ ሲሰራ አያለሁ
አዝማች · Chorus
በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ውድቀቱን ለሚሹ ለሚመትቱበት
በረከቱን ይዘው ሞት ለሚመኙለት
ከሰማይ የሆነ ትንቢትን ይዣለሁ
ለፃድቁ መልካም ይሆናል እላለሁ
አንበጣ አይደለሁም ትንሽ ምናምንቴ
ፈቃድን አልሰጠውም እንዲስቅ ጠላቴ
በዘመኔ ላይ መልካም መልካሙን እናገራለሁ
የኢየሱስ ወንጌል በህይወቴ ላይ ሲሰራ አያለሁ
አዝማች · Chorus
በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ለቅዱሳን ሁሉ ክፉ የመደባችሁ
ሥም እየጠራችሁ እርገሙ ብሏቸው
የተናገሩት ቃል ይሁን ለራሳቸው
ያጠመዱት ወጥመድ ዞሮ ይያዛቸው
አዝማች · Chorus
በእኔ ዘመን መልካሙን መልካሙን አያለሁ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ