እጁ መጣ
Eju meta
2009 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቀን ተቀጥሮ ለመሞቴ
ሊያበቃ ይህ ታሪኬ
ጀንበር ልትጠልቅ አዘቅዝቃ
ያለኝ ተስፋ ሊያበቃ ሲል
ቁጥር 2 · Verse 2
እጁ መጣ (፬x)
ጌታ መጣ (፬x)
እጁ መጣ ጌታ መጣ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ለብዙ ለብዙ ዘመናት ጦር ከጁ ያልተለየው
ወርውሮ ወርውሮ የማይስተው ሳኦል የተባለው
ዳዊት ላይ ወርውሮ ለምንድነው የሳተው
አዝኖለት አይደለም እግዚአብሔር ጋርዶት ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የዚህ አለም ገዢ በጥልቅ ተቀምጦ
ሲፎክር አየሁት የእኔ አይኔ ተከፍቶ
ሲፎክር ሰምቼ ልቤ ሲርድብኝ
ጌታ መንፈስ ቅዱስ እኔን ተናገረኝ
የፉከራ ድምፁን ሰምተህ ከምትፈራ
የተፃፈለትን ሂድ እና አንብበው
ቅዱሱን መጽሐፍ ገልጬ ሳነበው
የወንድሞች ከሳሽ ተጥሏል ነው እሚለው
አዝማች · Chorus
እጁ መጣ ጌታ መጣ (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የጠላቴ ውጥኑ እቅዱ
ተስፋ ያረገው ክፉ ወጥመዱ
ባዶ ውሎ ባዶ አደረ
በአምላኬ እቅድ ተሰበረ
ያሰበው አልተሳካም ያሰበው (፬x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ጳውሎስ ከባህር ላይ ከመርከብ አደጋ
ወደዳሩ ደርሶ እንደተረጋጋ
ብርድ ስለነበር እሳት እየሞቀ
ድንገት ከእጁ ላይ በእባብ ተነደፈ
ካሁን ካሁን አብጦ ይሞታል እያሉ
እዛው ይቀበራል ብለው ሲወያዩ
በእርጋታ መንፈስ እባቡን አራግፎ
ጌታን አገልግሏል ከእፉኝት ተርፎ
አዝማች · Chorus
እጁ መጣ ጌታ መጣ (፬x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ለብዙ ለብዙ ዘመናት ጦር ከጁ ያልተለየው
ወርውሮ ወርውሮ የማይስተው ሳኦል የተባለው
ዳዊት ላይ ወርውሮ ለምንድነው የሳተው
አዝኖለት አይደለም እግዚአብሔር ጋርዶት ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
እጁ መጣ ጌታ መጣ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ