ጉልበቴ
Gulbetie
2009 · ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በግብፅ የነበረውን የህዝቡን ጩኸት የሰማ ጌታ
ጊዜና ዘመን ጠብቆ ወደኔ መጣ
አዝማች · Chorus
በቃ አለው (፪x) ያን ክፉ
በቃ አለው ያን ክፉ
ጌታዬ ከልሎኝ በክንፉ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያቤቱታ ድምፄ ወደ ጆሮው ደርሶ
የምህረት ፊቱን ወደኔ መልሶ
ከጨቋኙ ገዢ ነፍሴን አላቋታል
ውስጤን በደስታ እንዲህ አስብሎታል አሄ
አዝማች · Chorus
አስባለሁ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ (፪x)
እላለሁ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በውርደቴ መንደር ክብር ያየሁበት
የቆሰለው ልቤ የተፈወሰበት (፪x)
እላለሁ እላለሁ እንደ እግዚአብሔር የለም አሜን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደ ወትሮው ሰላም አውለኝ ብዬ ስነሳ
የፈሮኦንን ጡብ ልሰራለት ከቤት ስወጣ
ያስገባሪዬን ገመድ ከላዬ ሊፈታልኝ
አምላኬ መጣ ያዘንኩበትን ቀን ቀጥሮልኝ
ግብፅን ለቅቄ ያን ቀን ስወጣ
ፈርኦን ሲያየኝ እንዲህ አልኩታ
ጉልበቴ (፪x)
ላዳነኝ ጌታ ነው ጉልበቴ
አትበላው ከሳሼ
አዝማች · Chorus
በግብፅ የነበረውን የህዝቡን ጩኸት የሰማ ጌታ
ጊዜና ዘመን ጠብቆ ወደኔ መጣ
በቃ አለው (፪x) ያን ክፉ
በቃ አለው ያን ክፉ
ጌታዬ ከልሎኝ በክንፉ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ