ሳየው
Sayew
2009 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ውስጤን ዝም ብሎ ይለኛል ደስ ደስ ደስ ደስ (X ፪)
ምን ሆነህ ነው ካሉኝ ኢየሱስ ኢየሱስ
ማን አገኘህ ላሉኝ ኢየሱስ ኢየሱስ
ሰላሜማ ደስታዬማ ኢየሱስ ነው ለኔ
ምንም ነገር የማይተካው ነው የዘላለሜ
አዝማች · Chorus
(ሳየው ካጎነበስኩበት ሳየው ቀና ቀና እላለሁ
ሳየው ምርኮ እንዳገኘ ሰው ሳየው በፊቱ እዘላለሁ) X ፪
ሳየው ሳየው ሳየው (፪)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁልጊዜ ሳዝን ስተክዝ የሚያውቁኝ
ሀዘኔ ተገፍፎ ደስ ብሎኝ አገኙኝ
እጅጉን ተገርመው አይን አይኔን እያዩኝ
ምን ብታገኝ ነው ደስ ያለህ እያሉ
ብር ነው? ወርቅ ነው? ምስጢሩን ንገረን
እንዲህ መለወጥህ በጣም ነው የገረመን
በማለት ጥያቄ ለእኔ ሲያቀርቡ
ብር ወርቅም አይደለም አንድ ነው ምስጢሩ
አዝማች · Chorus
ኢየሱሱ እየሱስ ነው ኢየሱስ ኢየሱስ ነው (X ፪)
ሰላሜማ ደስታዬማ ኢየሱስ ነው ለኔ
ምንም ነገር የማይተካው ነው የዘላለሜ
(ሳየው ካጎነበስኩበት ሳየው ቀና ቀና እላለሁ
ሳየው ምርኮ እንዳገኘ ሰው በፊቱ እዘላለሁ) X ፪
ሳየው ሳየው ሳየው ሳየው (X ፪)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰው አለኝ ቢለኝ የእርካታ ምንጭ
የደስታ ምንጭ ልክ ነው እሱማ
ከአምላኬ አይበልጥም አንጂ ከኢየሱስ አይበልጥም እንጂ (X ፫)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ