ስሙኝማ
Semugnema
2009 · ትራክ 9 · 6:07 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሰነፍ ምክር ልቡ ተውጦ
የጽድቅን መንገድ የሄደ አቋርጦ
የሥጋን ለባሽ ደጅ እየጠና
ዛሬም ይኖራል ሆኖ ጥገኛ
ያ ሰው ያ ሰው
ፊቱን ብፈልግ ደጁን ብጠና
ኧረ አትዘን ብሎ ያረገኝ ቀና
ዛሬም የሙጥኝ እርሱን እላለሁ
የእኔስ ደጋፊ ጌታ እግዚአብሔር ነው
ካለው ተወለድ ወይ ካለው ተጠጋ
የሚለው ተረት መች ይገባኛል
ኢየሱስ ካለኝ ሁሉም እንዳለኝ መንፈስ ነግሮኛል
በሰው የወጣ በሰው ይወርዳል
የተሰጠውም በመንገድ ያልቃል
የእኔ ኢየሱስ ግን በምድረ በዳ ምንጭን ያፈልቃል
አዝማች · Chorus
(ስሙኝማ) የእኔ ደጋፊ
(ስሙኝማ) ካለልኝ ከጐኔ
(ስሙኝማ) ማንም ሰው ባይኖረኝ
(ስሙኝማ) ምን ሊጨንቀኝ እኔ
ሁሉን የሚያስንቅ በልጦ ሚተካ
የልቤ ወዳጅ አለለኝ ጌታ
አለልኝ የእኔ ጌታ አለልኝ
አለልኝ ኢየሱሴ አለልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
በልምምጥ ቃል በአባባይ ቋንቋ ተቀለጣጥፎ ሰው የተጠጋ
ፍጻሜ ሳይደርስ አንገቱን ደፍቶ ቆሟል እዛጋ
የአምላኩን ፊት እየፈለገ
ጌታን በመፍራት ተግቶ የኖረ
ላይቆም ይሄዳል የጌታን ማዳን እየሰበከ
ዘንድሮ ሆኗል ምላስ ላላቸው
የሰው ደጋፊ ለበዛላቸው
ብለው ለሚሉ ጌታ ልኮኛል እንዲህ እንድላቸው
እነ ኤልያብ ሰልፍ እንደያዙ
እኔን ብቀባኝ ብለው ሲጓጉ
ጌታ የደገፈው ዳዊት ተቀባ እነሱ እያዩ
አዝማች · Chorus
(ስሙኝማ) የእኔ ደጋፊ
(ስሙኝማ) ካለልኝ ከጐኔ
(ስሙኝማ) ማንም ሰው ባይኖረኝ
(ስሙኝማ) ምን ሊጨንቀኝ እኔ
ሁሉን የሚያስንቅ በልጦ ሚተካ
የልቤ ወዳጅ አለለኝ ጌታ
አለልኝ የእኔ ጌታ አለልኝ
አለልኝ ኢየሱሴ አለልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
በሥጋ ለባሽ ዓይኑን የጣለ
አለኝ እከሌ ለሁሉ ያለ
የተመካበት ድንገት ሲሰበር ዓይኔ ይሄን አየ
ከዘመድ አዝማድ ዓይኑን ያነሳ
በአምላኩ ታምኑ ከዑር የወጣ
አንዱን ደጋፊ አብርሃም ይዞ ከቶ ምን አጣ
አዝማች · Chorus
(ስሙኝማ) የእኔ ደጋፊ
(ስሙኝማ) ካለልኝ ከጐኔ
(ስሙኝማ) ማንም ሰው ባይኖረኝ
(ስሙኝማ) ምን ሊጨንቀኝ እኔ
ሁሉን የሚያስንቅ በልጦ ሚተካ
የልቤ ወዳጅ አለለኝ ጌታ
አለልኝ የእኔ ጌታ አለልኝ
አለልኝ ኢየሱሴ አለልኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ