ይቤዠኛል
Yebezegnal
2009 · ትራክ 4 · 5:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰው ከሆነበት አስደንጋጭ ወሬ
ወየው ከሚያሰኝ ከክፉ ፍሬን አሄ
ሳልርበተበት ሳልል የት ልግባ
ከዓይኔ ሳይወጣ የሃዘን እንባ
አዝማች · Chorus
ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል
ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ነፍሴ ማን አለና የቱን ለማን ስትል
ድንገት ስታጣቸው ቃል የገቡላትን
እጆቹን ዘርግቶ አቅፎ የተቀበላት
በጣም በጭንቋ ቀን አላት የሚቤዣት (፪x)
አዝማች · Chorus
ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል
ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እተርፋለሁ አላልቅም አብሬ
የሚያድነኝ ገብቷል በመንደሬ
የሚያድነኝ ገብቷል በሰፈሬ
ለኃጢአተኛው የሚመጣው ዱላ
የጻድቁን ቤት አይነካምና
የመንፈሱን ቤት አይነካምና
እሩትን ከተቤዣት ከቡሄዝ በልጦ
ለተሻለው ኪዳን ለእኔ ዋስ የሆነው
ልቤን የጣልኩበት ጌታ
በጭንቄ ደራሽ ነው ሚያስመካ (፪x)
እተርፋለሁ አላልቅም አብሬ
የሚያድነኝ ገብቷል በመንደሬ
የሚያድነኝ ገብቷል በሰፈሬ
ለኃጢአተኛው የሚመጣው ዱላ
የጻድቁን ቤት አይነካምና
የመንፈሱን ቤት አይነካምና
አዝማች · Chorus
ይቤዠኛል ያልኩት ይቤዠኛል
ያድነኛል ያልኩት ያድነኛል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ