Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አመልካለሁ

Amelkalehu

ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አመልካለሁ እጆቼን አንስቼ

ጥያቄዬን ሁሉ እረስቼ

ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ

ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ

ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ

ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ (፪x)

ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (፬x)

ሁልጊዜ ሥምህን እጠራለሁ እጠራለሁ

ኢየሱስ ኢየሱስ እልሃለሁ እልሃለሁ (፪x)

እልሃለሁ እልሃለሁ ፣ እልሃለሁ እልሃለሁ

ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (፬x)

እንደ ማር ጣፈጠኝ ሥምህ አፌ ላይ

ከሥምህ የሚበልጥ ሥም ይገኛል ወይ (፪x)

ሥሞች ተሰብስበው ለሥምህ ሰገዱ

ከሥማቸው ይልቅ ሥምህን ወደዱ (፪x)

ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (፬x)

ምስጢሩ ምንድን ነው ምስጢሩ ይኼ ነው

ሥሙን ያስወደደው በሃሪው እኮ ነው (፪x)

ሥሙና ሕይወቱ አንድ ላይ ይሄዳል

እንደ ኢየሱስ ያለ ከወዴት ይገኛል (፪x)

ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (፬x)

እሺ ባይነትህ ታዛዥነትህ

ክብርህን ለመጣል ክብር መጣልህ (፪x)

ዝቅ ዝቅ ማለትህ ከፍ ከፍ አድርጐሃል

ከሥሞች የሚበልጥ ሥምን አሰጥቶሃል (፪x)

ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (፬x)

አመልካለሁ እጆቼን አንስቼ

ጥያቄዬን ሁሉ እረስቼ

ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ

ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ

ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ

ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ

ኦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ (፬x)

ምነው ነፍሴ እንደ ውኃ በሆንልኝ

አምላኬ ፊት እንደ ጅረት ቢፈስልኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ