እንዳንተ ያለ የለም
Endante Yale Yelem
ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔርን አሰብኩት ደስም አለኝ
ቸርነቱን አሰብኩት ደስም አለኝ
ፍቅሩንም አሰብኩት ደስም አለኝ
ደግነቱን አሰብኩት ደስም አለኝ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አንዳንተ ያለ የለም (፪x)
አምላኬ አንዳንተ ያለ የለም
ጌታዬ አንዳንተ ያለ የለም
ቁጥር 2 · Verse 2
አጥንቶቼ ሁሉ እንደዚህ ይሉሃል
እንዳንተ ያለ ማነው ኦሆሆ
ብለው ያመልኩሃል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኧረ እንደው ምናለ ቃላት ባገኘሁኝ አሃሃ
የልቤን የውስጤን ዘርዝሬ መናገር በቻልኩኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔርን አሰብኩት ደስም አለኝ
ቸርነቱን አሰብኩት ደስም አለኝ
ፍቅሩንም አሰብኩት ደስም አለኝ
ደግነቱን አሰብኩት ደስም አለኝ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አንዳንተ ያለ የለም (፪x)
አምላኬ አንዳንተ ያለ የለም
ጌታዬ አንዳንተ ያለ የለም
ቁጥር 5 · Verse 5
ብዙዎች ኃይል አግኝተው ኦሆሆ
ብዙ ነገር አሉህ አሃሃ
አንተ ግን ትበልጣለህ አሃሃ
እስከዛሬ ካሉህ ኦሆሆ (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤቱ አንዳንተ ያለ የለም (፪x)
አምላኬ አንዳንተ ያለ የለም
ጌታዬ አንዳንተ ያለ የለም
ቁጥር 6 · Verse 6
ኧረ እንደው ምናለ ቃላት ባገኘሁኝ
የልቤን የውስጤን ዘርዝሬ መናገር በቻልኩኝ
አምላኬ ጌታዬ የእጄን ሰንሰለት በጠሰው (፬x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ድንቅ ነው ግርማው ውበቱ
እግዚአብሔር/አምላኬ አቤቱ አቤቱ (፪x)
ቁጥር 8 · Verse 8
ነፍስም አልቀረልኝ አንተን አይቼ
በፊትህ ወደኩኝ ድምጽህን ሰምቼ
ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል
ሞገስ በከንፈርህ ጌታ ይፈሳል
ድንቅ ነው ግርማው ውበቱ
እግዚአብሔር/አምላኬ አቤቱ አቤቱ (፪x)
ቁጥር 9 · Verse 9
ከፀሐይ ሰባት እጅ ያበራል ፊቱ
ከአይምሮ በላይ ነው አንተን ማየቱ
ሊታይ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ያለው
ባህሪው ውበቱ አስደናቂ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ