Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አትለዋወጥም

Atelewawetem

ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የነበረ ያለ የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው

ፍጥረት ሁሉ በመደነቅ የሚከታተለው (፪x)

የነበረው ሁሉ በነበር አለቀ

የድሮ ታሪክ ነው እጅጉን የራቀ

ድሮም ዛሬም ነገም ነበረ ያልሆነው

በዘመናት መሃል እግዚአብሔር ብቻ ነው

የነበረ ያለ የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው

ፍጥረት ሁሉ በመደነቅ የሚከታተለው (፪x)

አንተ አትለዋወጥም አሃ

አንተ ኃይልህ አይቀንስም አዎ

አንተ ዘመንህ አያልቅም አሃ

አንተ ጉልበትህ አይዝልም አሃ (፪x)

አትለዋወጥም አሃሃ (፲፮x)

እኔ እኮ የሚገርመኝ ሁልጊዜ ያው መሆንህ ነው (፪x)

እኔ እኮ የሚደንቀኝ ሁልጊዜ ያው መሆንህ ነው (፰x)

አንተ አትለዋወጥም አሃ

አንተ ኃይልህ አይቀንስም አዎ

አንተ ዘመንህ አያልቅም አሃ

አንተ ጉልበትህ አይዝልም አሃ (፪x)

አትለዋወጥም አሃሃ (፲፮x)

አይተናል አዎ ኃያላን ሲያልፉ

አይተናል አዎ ብርቱዎች ሲደክሙ

አይተናል አዎ ቁንጅና ሲያልፍ

አይተናል አዎ ውበት ሲረግፍ (፪x)

አንተ አትለዋወጥም አሃ

አንተ ኃይልህ አይቀንስም አዎ

አንተ ዘመንህ አያልቅም አሃ

አንተ ጉልበትህ አይዝልም አሃ (፪x)

አትለዋወጥም አሃሃ (፲፮x)

እነ ኃያላን እነ አለቆች

እነ ነገሥታት እነ አልሞት ባዮች

አንድ በአንድ ሁሉም ሁሉም አለፉ

እያየናቸው ከምድር ላይ ጠፉ (፪x)

አንተ ግን አትለዋወጥም አሃ

አምላኬ አትለዋወጥም አሃ

አምላክህ አይለዋወጥም አሃ

አምላክሽ አይለዋወጥም አሃ

እርሱ እኮ አይለዋወጥም አሃ

አምላኬ አይለዋወጥም አሃ

አምላክህ አይለዋወጥም አሃ

አምላክሽ አይለዋወጥም አሃ

አትለዋወጥም አሃሃ (፲፮x)

ትልቅ ነህ ሰፊ ነህ ጥልቅ ነህ ረቂቅ (፪x)

በዓይኔ በብረቱ አይቻለሁ አሃ

ትልቅነትህን አይቻለሁ አሃ

የማይሆነው ሲሆን አይቻለሁ አሃ

ያለቀ ሲጀምር አይቻለሁ አሃ (፪x)

ስለዚህ/እኔማ አምልክሃለሁ

ወገቤን ታጥቄ አምልክሃለሁ

ልክህን አውቄ አምልክሃለሁ

ልክህን አውቄ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ