አይበቃም
Aybeqam
ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱስ የምለዉ
የጥያቄዬ መልስ የሆነዉ
ልቤ ያረፈበት ምወደው
እፎይ የምልበት እርሱ ነዉ (፪x)
አይበቃም እንደዚህ ብለህ
አይበቃም እንደዚያም ብለህ
አይበቃም እኔ ባመልክህ
አይበቃም አይበቃም ፣ አይበቃም አይበቃም
አምላክ ሆይ እንደ አንተ ያለ የለም (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የማለዳ ጨረር የጠዋት ብርሃን
አንተ በደስታ አሞከው ልቤን
ህልሜን ልተርከው ከእንቅልፌ ስነቃ
አረጋገጥክልኝ ሌሊቱ እንዳበቃ (፪x)
ምን ዓይነት አምላክ ነህ
ምን ዓይነት ንጉሥ ነህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ኢየሱስ የምለዉ
የጥያቄዬ መልስ የሆነዉ
ልቤ ያረፈበት ምወደው
እፎይ የምልበት እርሱ ነዉ (፪x)
አይበቃም እንደዚህ ብለህ
አይበቃም እንደዚያም ብለህ
አይበቃም እኔ ባመልክህ
አይበቃም አይበቃም ፣ አይበቃም አይበቃም
አምላክ ሆይ እንደ አንተ ያለ የለም (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ማምለክ አየሬ ነው ሳላመልክ አልኖርም
ከሁኔታ ጋር አላያይዘውም
ተመስገን ሳልልህ ሥምህን ሳልቀድስ
እንዴት እኖራለሁ እኔ ሳልተነፍስ (፪x)
ምን ዓይነት አምላክ ነህ
ምን ዓይነት ንጉሥ ነህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አምላክ ሆይ እንደ አንተ ያለ የለም (፬x)
አይበቃም እንደዚህ ብለህ
አይበቃም እንደዚያም ብለህ
አይበቃም እኔ ባመልክህ
አይበቃም አይበቃም ፣ አይበቃም አይበቃም
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔር ሆይ ስለ ሥምህ አመልክሃልሁ (፪x)
እግዚአብሔር ሆይ ስለ ራስህ አመልክሃልሁ አሃ (፪x)
እግዚአብሔር ሆይ ስለ ሥምህ አመልክሃልሁ (፪x)
እግዚአብሔር ሆይ ስለ ራስህ አመልክሃልሁ አሃ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ