Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምልጥ

Amlet

2002 · ትራክ 5 · 4:19 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የዚህ ዓለም ክብር ያልፋል በእሳት ተቃጥሎ

ምን ትጠብቃለህ ወንድሜ (ና ተሎ)፪

(ና ተሎ) (፪x)ኢየሱስ ይመጣል

ሕይወት ወይም ሞት ምረጥ ከሚመጣው ቁጣ አምልጥ

ሕይወት ወይም ሞት ምረጥ ከሚመጣው ቁጣ አምልጥ

(አምልጥ) (፫x)

ከኖህ ዘመን የከፋ ይሆናል ታላቅ ጥፋት

ወደ ኢየሱስ ናና ሕይወትህን (አትርፋት) (፪x)

(አትርፋት) (፪x) አትሂድ ወደ ሳት

ሕይወት ወይም ሞት ምረጥ ከሚመጣው ቁጣ አምልጥ

ሕይወት ወይም ሞት ምረጥ ከሚመጣው ቁጣ አምልጥ

(አምልጥ) (፫x)

የሰው ሕይወት እንደ ጤዛ መሆኑን ተረዳ

በሞት ይወሰዳል አይተነው (ማለዳ) (፪x)

(ማለዳ) (፪x) ወንድሜ አትጐዳ

ሕይወት ወይም ሞት ምረጥ ከሚመጣው ቁጣ አምልጥ

ሕይወት ወይም ሞት ምረጥ ከሚመጣው ቁጣ አምልጥ

(አምልጥ) (፫x)

ስልጣንህ ዕውቀትህ ገንዘህ አያድኑህም

ከመቃብር ወዲያ አይከተሉህም

(ተው ወንድም) (፪x) ወደ ሞት አታዝግም

ሕይወት ወይም ሞት ምረጥ ከሚመጣው ቁጣ አምልጥ

ሕይወት ወይም ሞት ምረጥ ከሚመጣው ቁጣ አምልጥ

(አምልጥ) (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ