Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንደገና

Endegena

2002 · ትራክ 4 · 4:27 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በደሙ ተቀድሰን የምሥጋና ልብስ ለብሰን

ጠላታችንም እያየን ምሥጋና ለርሱ እንሰዋለን

(እንሰዋለን) (፭x) ጠላታችን ባይኑ እያየን

ጀሮው እየሰማ (እንሰዋለን) (፬x)

(እንደገና) (፪x) ጌታ ለአንተ ምሥጋና ኢየሱስ እጥፍ ምሥጋና

(እንደገና) (፪x) ጌታ ይሄው ምሥጋና ለአንተ እልፍ ምሥጋና

እልፍ አእላፍ ሁላችሁ ይከፈት እንደበታችሁ

ለንጉሡ ምሥጋናን አምጡ ወድቃችሁ ክብርን አምጡ

(ክብርን ስጡ) (፭x) (ምሥጋና አምጡ) (፪x)

ለዘለዓለም እንደርሱ የለም

(እንሰዋለን) (፭x)

(እንደገና) (፪x) ጌታ ለአንተ ምሥጋና ኢየሱስ እጥፍ ምሥጋና

(እንደገና) (፪x) ጌታ ይሄው ምሥጋና ለአንተ እልፍ ምሥጋና

ታሪኩ የተለወጠ በቀኙ የተቀመጠ

ከእኔ ጋራ ይሁንና እንከምር ክብር ምሥጋና

(ክብር ምሥጋና) (፭x) ለርሱ ነውና

ለዘለዓለም እንደ እርሱ የለም

(እንሰዋለን) (፭x)

(እንደገና) (፪x) ጌታ ለአንተ ምሥጋና ኢየሱስ እጥፍ ምሥጋና

(እንደገና) (፪x) ጌታ ይሄው ምሥጋና ለአንተ እልፍ ምሥጋና

የዜማ ዕቃ ሁሉ ይውጣ ለጌታ መልካም ድምጽ ያውጣ

ጉባኤው ይድመቅ በልልታ ኢየሱስ ብቻውን ጌታ

(ብቻውን ጌታ) (፭x) (ሁሉን የረታ) (፪x)

ለዘለዓለም እንደ እርሱ የለም

(እንሰዋለን) (፭x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ