Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምሥጋና ይዤ መጣሁ

Mesgana Yezie Metahu

2002 · ትራክ 7 · 8:14 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

<poem>

ምሥጋና አምልኮ ይዤ መጣሁ

አንተን የሚመስል አጣሁ

ተወደስ ተቀደስ ለዘለዓለም

የሚወዳደር የለም (አንተን የሚመስል የለም) (፬x)

የፀሐይ ድምቀትዋ የምድር ስፋቷ

የውቂያኖስ ጥልቀት የሰማይ ርቀት

አንተ ባለግርማ ከማን ላወዳድርህ

ወጥቸ ወርጀ አጣሁ የሚመስልህ

ክረምት አለፈ በጋው መጣ

አንዱ ወረደ ሌላው ወጣ

ግን እስከዛሬ ሕያው የሆነው

የእኛው ኢየሱስ ብቻ ነው

(አማኑኤል ብቻ ነው) (፪x)

የእኛ ጌታ ብቻ ነው

የእኛ ኢየሱስ ብቻ ነው

ምሥጋና አምልኮ

የነፋስ ሽውታ የእጽዋት ሽታ

የወንዝ የጅረቱ የአእዋፍ የአራዊቱ

አድንቄ አድንቄ ሁሉን በየተራ

መጨረስ አልቻልኩም ጌታ የአንተን ስራ

ክረምት አለፈ በጋው መጣ

አንዱ ወረደ ሌላው ወጣ

ግን እስከዛሬ ሕያው የሆነው

የእኛው ኢየሱስ ብቻ ነው

(አማኑኤል ብቻ ነው) (፪x)

የእኛ ጌታ ብቻ ነው

የእኛ ኢየሱስ ብቻ ነው

ምሥጋና አምልኮ

የሰው ልጆች ውበት የጀግኖቹ ጉልበት

የባለጸጋው ፍርድ የጠቢባን ጥበብ

ከማን ላወዳድረው ጌታ የአንተን ዝና

በዘመናት ሁሉ ብቻህን ገናና

ክረምት አለፈ በጋው መጣ

አንዱ ወረደ ሌላው ወጣ

ግን እስከዛሬ ሕያው የሆነው

የእኛው ኢየሱስ ብቻ ነው

(አማኑኤል ብቻ ነው) (፪x)

የእኛ ጌታ ብቻ ነው

የእኛ ኢየሱስ ብቻ ነው

ምሥጋን አምልኮ

ቅኔው ማህሌቱ የሙዚቃው ስልቱ

ስዕሉም ተኩሎ ማን አንተን አክሎ

ቃላት አይገልጹህም ታላቅነትህን

በገባን መጠን እናክብር ስምህን

ክረምት አለፈ በጋው መጣ

አንዱ ወረደ ሌላው ወጣ

ግን እስከዛሬ ሕያው የሆነው

የእኛው ኢየሱስ ብቻ ነው

(አማኑኤል ብቻ ነው) (፪x)

የእኛ ጌታ ብቻ ነው

የእኛ ኢየሱስ ብቻ ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ