እግዚአብሔር ነው በሰልፍ ኃያል
Egziabhier New Beself Hayal
2002 · ትራክ 6 · 5:57 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እናንተ መኳንት በሮችን ክፈቱ
የዘለዓለም ደጆች ይከፈቱ
(የክብር ንጉሥ ይግባ) (፫x) ኢየሱስ ጌታ ይግባ
ፊተኛ ኋለኛ አልፋና ኦሜጋ ነው
ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለው
ነገሥታትን ሁሉ ብቻውን ያሸነፈ
ህዝቡን ከሞት ያተረፈ
አዝማች · Chorus
(እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል
እግዚአብሄር ነው በሰልፍ ሃያል
እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል) (፪x)
እናንት መኳንት
ቁጥር 2 · Verse 2
በአምላካችን ፈት በኃይሉ ማን ይቆማል
ነጐድጓድ ድምጹን ማን ይሰማል
ተራራን በግርማው እንደሰም ያቀለጠው
ምድረ በዳውን ያናወጠው
አዝማች · Chorus
(እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል
እግዚአብሄር ነው በሰልፍ ሃያል
እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል) (፪x)
እናንት መኳንት
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር ተዋጊ ስሙም ደግሞ እግዚአብሔር ነው
የሰይጣንን ሰልፍ የበተነው
ኃይሉ እጅግ ታላቅ ነው በደመናት ላይ ይራመዳል
ትቢተኞችን ያዋርዳል
አዝማች · Chorus
(እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል
እግዚአብሄር ነው በሰልፍ ሃያል
እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል) (፪x)
እናንት መኳንት
ቁጥር 4 · Verse 4
ክብሩን ሊያሳዬን ሥጋ ለብሶ የተገለጠው
ከአርያም ቃሉን የሰጠው
በሞቱ ሞታችንን ለዘለዓለሙ የገደለው
አውሬውን ወደሳት የጣለው
ቁጥር 5 · Verse 5
(እግዚአብሔር(ኢየሱስ) ነው ብርቱና ኋያል
እግዚአብሄር(ኢየሱስ) ነው በሰልፍ ሃያል
እግዚአብሔር(ኢየሱስ) ነው ብርቱና ኋያል) (፪x)
አዝማች · Chorus
እናንት መኳንት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ