Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከሸለቆ ወጣ

Kesheleqo Weta

2002 · ትራክ 9 · 6:50 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንተ አገልጋይ ጌታን የምትወደው

በድካም ሕይወት ያለኸው

ከሸለቆ ውጣ ና ና

ዛሬም ኢየሱስ(ጌታ) ይወድሃልና

ይጠራሃልና

እርሻውን አርሰህ ጐልጉለህ ለመከሩ ደክመህ

ስለወንጌል ብለህ ብዙ ዋጋ ከፍለህ

(አሁን ምነው ደከምህ አዝመራው ሲቃረብ

የዚች ዓለም አንድ ቀን አያልቅም ) (፪x)

አንተ አገልጋይ

ተስፋ አይቆረጥ በጌታ ምህረቱ ብዙ

ዓለም አድክማቸው ለደነዘዙ

(የደከመን ጉልበት እንደ ንስር ያድሳል

ወደ ቀደመው ክብር ዳግም ይመልሳል) (፪x)

አንተ አገልጋይ

ዘመኑ ሲቃረብ ክፉንም ዙሪያህ

ሰው የላዩን ትቶ የምድሩን ያስባል

(ነገር ግን ሁሉ ከንቱ ነው ንፋስን መከተል

የከበረው ብድራት ኢየሱስን ማገልገል) (፪x)

አንተ አገልጋይ

ወንድሜ ሆይ ስለምን ተስፋ ቆረጥክ ጌታ እኮ ይወድሃል

ያውም እስከ መስቀል ሞት ዛሬ ና ተነስ ጌታ ሳይመጣ

አገልግለው

አንተ መስክረህላቸው ያስተማርካቸው

ዛሬ አድገው ቤቱ አገልጋዮች ናቸው

(ዘወትር በጌታ ፊት ይጸልዩልሃል

እግዚአብሔርም ታማኝ ነው አንተን ያስብሃል) (፪x)

እግዚአብሔር እንደ ሳምሶን አንዴ ያስብሃል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ