የዜማ ጊዜ ደረሰ
Yeziema Gizie Derese
2002 · ትራክ 2 · 5:43 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ወይን አብቦ አፈራ
በለስ መልሶ ጐመራ
የዜማ ጊዜ ደረሰ
አምላኬ/እግዚአብሔር ኃይሌን አደሰ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጠላት ስማ እፈር እፈር
ሰይጣን ስማ እፈር እፈር
ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሌ እየዞርክ ዙሪያዬን
ስታጣጥለው ተስፋዬን
የታመንኩት ወዳጅ ደረሰና
አንደበቴን ሞላው በምሥጋና
የታመንኩት ኢየሱስ ደረሰና
እኔንም አቆመኝ እንደገና
አዝማች · Chorus
ጠላት ስማ እፈር እፈር
ሰይጣን ስማ እፈር እፈር
ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ነፍስ ዘራ የሞተ
ከጉድጓድ የተከተተ
የሰማይ ደጆች ተከፈቱ
ለቤቴ በዛ ተዓምራቱ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጠላት ስማ እፈር እፈር
ሰይጣን ስማ እፈር እፈር
ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጌታን የሚጠባበቁ
ይከብራሉ እንጂ አይወድቁ
ኃይላቸውንም ያድሳሉ
የጠላትን ደጅ ይወርሳሉ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጠላት ስማ እፈር እፈር
ሰይጣን ስማ እፈር እፈር
ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር
ቁጥር 5 · Verse 5
ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ