አያለሁ
Ayalehu
2006 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የውስጤ የእኔ ፍላጐቴ
ክብርህ ነው የሁሌ ጥማቴ
ለሃገር ለወገን መፍትሄ ስንሆን
የተወሰድብን ሲመለስልን
ይሄ ነው ጥማቴ የውስጤ ርሃቤ
ይህንን አያለሁ አምኖሃል ልቤ
የቤትህ ስርአት ተበላሽቶ
ተው የሚል የሚመልሰን ጠፍቶ
ይህ ሁሉ አካሄድ ያቆምና
አያለሁ ታድሶ እንደገና
አዝማች · Chorus
አያለሁ ክብርህ ቤትህን ሞልቶ
አያለሁ ያዘነው ተጽናንቶ
አያለሁ የፈረሰው ቅጥር
አያለሁ ታድሶ በክብር
አያለሁ ሰው ሁሉ ሲገረም
አያለሁ ትንቢቱም ሲፈጸም
ቁጥር 2 · Verse 2
ከጥንቱ የነበረው ሃይልህ
ለትውልድ መፍትሄ የነበርህ
አያለሁ የአንተ ክብር ሲያበራ
በእጥፍ በዚህ ዘመን ሲሰራ
አዝማች · Chorus
አያለሁ ክብርህ ቤትህን ሞልቶ
አያለሁ ያዘነው ተጽናንቶ
አያለሁ የፈረሰው ቅጥር
አያለሁ ታድሶ በክብር
አያለሁ ሰው ሁሉ ሲገረም
አያለሁ ትንቢቱም ሲፈጸም
ቁጥር 3 · Verse 3
ሕይወቱ ኑሮው የጨላለመ
በሃዘን ልቡ የደካከመ
አያለሁ የአንተ ክብር ሲመጣ
ጥያቄ ነገር ሁሉ ሲፈታ
አዝማች · Chorus
አያለሁ ክብርህ ቤትህን ሞልቶ
አያለሁ ያዘነው ተጽናንቶ
አያለሁ የፈረሰው ቅጥር
አያለሁ ታድሶ በክብር
አያለሁ ሰው ሁሉ ሲገረም
አያለሁ ትንቢቱም ሲፈጸም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ