Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ስለ ምህረቱ

Sele Meheretu

2006 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስለ ምህረቱ ስለ እርሱ ዝና

ሰምቼ መጣሁ ሁሉን ተውኩና

ከሰማሁት በላይ አዩት ዐይኖቼ

እርሱ ጋር ቀረሁ ሕይወት አግኝቼ (፪x)

እርሱ ጋር ቀረሁ ሰላም አግኝቼ

ነፍሴ የወደደችው እርሱን

አይሆንላትም ሌላ ነገረ

ከእርሱ ጋራ ይዟታል ፍቅር

የለም አለች ከቶ እንደእግዚአብሔር

ቸርነቱ ምህረቱ የበዛ

አይገኝም የለም እንደጌታ

አየሁ ምህረቱን ፤ አየሁ ቸርነቱን

አየሁ ለተጠጋው ፤ አየሁ ሰው መውደዱን

አየሁ ሁልጊዜ ፤ አየሁ ከእኔ ጋራ

አየሁ እንደማይተወኝ ፤ አየሁ እሱን ስፈራ

ለጌታ ለቸርነቱ ፤ ለጌታ ምሥጋናን አምጡ

ለጌታ ስለሚገባው ፤ ለጌታ ለጌትነቱ

ለጌታ ይዘመርለት ፤ ለጌታ ይሁን ምትሉ

ለጌታ ለቸሩ ጌታ ፤ ለጌታ እስኪ እልል በሉ

ለጌታ ከዚህም በላይ ፤ ለጌታ ለእርሱ ቢሰዋ

ለጌታ ስለሚገባው ፤ ለጌታ አዳኝ ነውና

ስለ ምህረቱ ስለ እርሱ ዝና

ሰምቼ መጣሁ ሁሉን ተውኩና

ከሰማሁት በላይ አዩት ዐይኖቼ

እርሱ ጋር ቀረሁ ሕይወት አግኝቼ (፪x)

እርሱ ጋር ቀረሁ ሰላም አግኝቼ

ያ ጠላቴ ሊያጠፋኝ ሲያቅድ

በየቀኑ ወጥመዱን ሲያጠምድ

ቢሆንለት ሕይወቴን ሊያጠፋ

ሳያቋርጥ እጅግ ብዙ ለፋ

ኢየሱሴ ከእኔ ጋር ነበረ

የጠላቴም ወጥመድ ተሰበረ

አየሁ ምህረቱን ፤ አየሁ ቸርነቱን

አየሁ ለተጠጋው ፤ አየሁ ሰው መውደዱን

አየሁ ሁልጊዜ ፤ አየሁ ከእኔ ጋራ

አየሁ እንደማይተወኝ ፤ አየሁ እሱን ስፈራ

ለጌታ ለቸርነቱ ፤ ለጌታ ምሥጋናን አምጡ

ለጌታ ስለሚገባው ፤ ለጌታ ለጌትነቱ

ለጌታ ይዘመርለት ፤ ለጌታ ይሁን ምትሉ

ለጌታ ለቸሩ ጌታ ፤ ለጌታ እስኪ እልል በሉ

ለጌታ ከዚህም በላይ ፤ ለጌታ ለእርሱ ቢሰዋ

ለጌታ ስለሚገባው ፤ ለጌታ አዳኝ ነውና

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ