የእኔ ነህ
Yenie Neh
2006 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የእኔ ነህ (፫x) የማለውጥህ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታዬ የእኔ ነህ
የአንተው ነኝ (፫x) የማትተወኝ
እኔስ የአንተው ነኝ
ምርጫዬ ነህ የምወድህ
ከአንተ ሌላ ላልፈልግህ
ሕይወቴን ለወጥከው ወድሃለው አልከኝ
ሰላምን ሰጥተኽኝ ልጅህ አደረከኝ (፪x)
ማግኘት ማጣቴ መውጣት መውረዴ
አይለየኝም ከአንተ ፍቅር
እንዴት ይኬዳል ወዴት ይኬዳል
ከአንተ የሕይወት ቃል እያለ
አልመኘውም አልፈልገውም አንተ የሌለህበትን
ዘመኔ ይለቀ ከአንተ ጋር ሆኜ የእውነት እየወደድኩህ
እኔማ ወዴት እሄዳለው
እኔማ ማሄጃም የለኝም
እኔማ ከአንተ ተለይቼ
እኔማ ሕይወትምሰላም የለኝም (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ነህ (የእኔ ነህ) (፫x) የማለውጥህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታዬ የእኔ ነህ
(የአንተው ነኝ) የአንተው ነኝ (፫x) የማትተወኝ
(እኔስ የአንተው ነኝ)
አልፈልግም ከአንተ ሌላ
ምን ሊጠቅመኝ ምን ሊረባ
ተመችተኽኛል አንተ የእኔ ፍቅር
አንተው ትበቃለህ ብቻህን እግዚአብሔር (፪x)
ማግኘት ማጣቴ መውጣት መውረዴ
አይለየኝም ከአንተ ፍቅር
እንዴት ይኬዳል ወዴት ይኬዳል
ከአንተ የሕይወት ቃል እያለ
አልመኘውም አልፈልገውም አንተ የሌለህበትን
ዘመኔ ይለቀ ከአንተ ጋር ሆኜ የእውነት የወደድኩህ
(እኔማ) እኔማ ወዴት እሄዳለው
እኔማ ማሄጃም የለኝም
እኔማ ከአንተ ተለይቼ
እኔማ ሕይወትምሰላም የለኝም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ