የወደደህ ልቤ
Yewededeh Lebie
2006 · ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የወደደህ ልቤ በእኔ ማንነቴ
ድንቅ ድንቅ አየሁኝ በአንተ ሁሌ በሕይወቴ
በአንተ ተይዣለሁ ማነው የሚወስደኝ
ፍቅርህ እኔን ስቦኛል አልሰጋም ተመችተኽኛል (፪x)
አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ አንተን
ምሥጋናን ዝማሬ ማታ ቢሆን በቀን
እሰዋልሃለሁ የእውነቴን ሆኜ
ከአንተ ወዲያ ፍቅር አላየሁም እኔ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ለእኔ ሚሆነኝ ከአንተ ወዲያ
የለኝም አንተ ነህ የእኔ መመኪያ
በአንተ ሕይወትን እኔ አግኝቻለሁ
ኢየሱስ ለአንተ እዘምራለሁ
ያለምንም እኔን የወደደ
ፍቅር እንደ ጌታ የት አለ
ለሰው የሚያዝን የሚራራ
ኧረ እንደኢየሱስ የለም ሌላ
ታዲያ ለኢየሱስ ቢዘመር
የእርሱ ታላቅነት ቢነገር
እርሱ ከወደደው ይሄ ሁሉ
እዘምራለሁኝ በየቀኑ
አዝማች · Chorus
የወደደህ ልቤ በእኔ ማንነቴ
ድንቅ ድንቅ አየሁኝ በአንተ ሁሌ በሕይወቴ
በአንተ ተይዣለሁ ማነው የሚወስደኝ
ፍቅርህ እኔን ስቦኛል አልሰጋም ተመችተኽኛል (፪x)
አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ አንተን
ምሥጋናን ዝማሬ ማታ ቢሆን በቀን
እሰዋልሃለሁ የእውነቴን ሆኜ
ከአንተ ወዲያ ፍቅር አላየሁም እኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የእውነት የማይጠፋ ፍቅር ያለህ
እንደአንተ እንደጌታዬ የት አለ
እንደሰው የማትለዋወጥብኝ
አንተ ነህ ከጐኔ ለእኔ ያለኽኝ
ያለምንም እኔን የወደደ
ፍቅር እንደ ጌታ የት አለ
ለሰው የሚያዝን የሚራራ
ኧረ እንደኢየሱስ የለም ሌላ
ታዲያ ለኢየሱስ ቢዘመር
የእርሱ ታላቅነት ቢነገር
እርሱ ከወደደው ይሄ ሁሉ
እዘምራለሁኝ በየቀኑ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ