Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኑሮዬ በኪዳን ነው

Nuroyie Bekidan New

2006 · ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሃገር ምድር ሲናወጥ ሰው ሁሉ ሲታገል ለማምለጥ

እየባሰ ግር ግሩ ሕይወቴን ሊረብሽ ሊያስፈሩ

ለካ ቆሜ ሳስበው ኑሮዬ በኪዳን ነው

ኧረ ከእኔ ጋራ ያለው እርሱ እግዚአብሔር ነው

ኪዳን አለኝ የእውነትም ቃል አለኝ

ኢየሱስ ነው ልጁ ያደረገኝ

መመኪያዬ የእውነትም ተስፋዬ

እርሱ ላይ ነው መደገፊያዬ (፪x)

እንድጠፋ ፈልጐ ያ ክፉ ሊወጠኝ ሲጥር

አልገባውም መሰለኝ እንዳለኝ ሃይለኛ ቅጥር

ሕይወቴን ሊተናኮል ጠጋ ጠጋ ሲለኝ

ኪዳኑን የሚያከብረው እግዚአብሔር ወጣልኝ

እስኪ በል ተናገር አሉኝ

እንዴት ነው ሚረዳህ አሉኝ

ልናገር አፌን ሞልቼ

የመጣውን ከአባቶቼ

ያኔም አሁንም ይሰራል

አልፎም ያድነኛል

የተጻፈውን ሳምን የቃልኪዳኑን (፪x)

ኪዳን አለኝ የእውነትም ቃል አለኝ

ኢየሱስ ነው ልጁ ያደረገኝ

መመኪያዬ የእውነትም ተስፋዬ

እርሱ ላይ ነው መደገፊያዬ

በሕይወቴ ስፈራ ነገ ስለሚሆነው ሳላቅ

ነገ ስለሚሆነው አለኝ ተው አትጨነቅ

በነጻነት እንድትኖር ከአንተ ጋራ ነኝ አለኝ

ይሄ የእውነት ኪዳን እንዳልሰጋ አረገኝ

ኪዳን አለኝ የእውነትም ቃል አለኝ

ኢየሱስ ነው ልጁ ያደረገኝ

መመኪያዬ የእውነትም ተስፋዬ

እርሱ ላይ ነው መደገፊያዬ

እስኪ በል ተናገር አሉኝ

እንዴት ነው ሚረዳህ አሉኝ

ልናገር አፌን ሞልቼ

የመጣውን ከአባቶቼ

ያኔም አሁንም ይሰራል

አልፎም ያድነኛል

የተጻፈውን ሳምን የቃልኪዳኑን (፪x)

አለኝ ቃልኪዳን ከእርሱ ጋራ

አለኝ ቃልኪዳን እንዴት ልፈራ (፰x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ