ይሄውና ልቤ
Yehiewena Lebie
2006 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ልቤን ይኽው እያት ወደ አንተ መልሳት
ልቤን ይኸው እያት እንደ አንተ አድርጋት
በሰው ልብ ብዙ ሃሳብ ምኞት ይገኛል
ዘወትር ከራሱ ጋር ሁሌ ያወራል
አንደኛው ስለምድር ሁሌ ያስባል
ያ ደግሞ ሰማያዊውን ይናፍቃል
ይህ ልቤ የሚመኘው አንተን ካልሆነ
መኖሩ ትርጉም የለው ያው ከንቱ ሆነ
አዝማች · Chorus
(ይሄውና ልቤ) በአንተ ይሞላ አንተን ይናፍቅ አንተን ይጠማ
(ይሄውና ልቤ) የእኔ አትሁን የአንተ አድርጋት ውሰዳትና
(ይሄውና ልቤ) እባክህ ልጄ ልብህን ስጠኝ ብለሃልና
(ይሄውና ልቤ) እስቲ ለውጣት የአንተ ዐይነት ልብ አድርገህ ቃኛት
(ይሄውና ልቤ)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘምሮ አጨብጭቦ ዘሎ ይወጣና
ያለቅሳል እንደገና ቤቱ ይገባና
በምድር ብዙ አሉ ልብ የሚጐዱ
መሽገው በጨለማ የሚናደፉ
ጠብቃት ይህቺ ልቤ እንዳትጐዳ
አበርታኝ ልቤ ሁልጊዜ በአንተ ትጽና
አዝማች · Chorus
(ይሄውና ልቤ) በምድር አሉ ከጐኔ ሆነው ልብ የሚገድሉ
(ይሄውና ልቤ) ሊያሳዝኗት ልቤን ለመጣል የሚማማሉ
(ይሄውና ልቤ) እኔ ከያዝኳት በትንሽ ነገር ትሸነፋለች
(ይሄውና ልቤ) አንተ ከያዝካት ሁልጊዜ ደስታ ሁሌ ብርቱ ነች
(ይሄውና ልቤ)
ቁጥር 3 · Verse 3
ልቤን ይኽው እያት ወደ አንተ መልሳት
ልቤን ይኸው እያት እንደ አንተ አድርጋት
አምላኬ ጌታዬ ነህ ገዢዬ ብዬ
ግን ሌላ ነገር በልቤ ላይ አዝዬ
ወንድሜን አብሮኝ ያለውን እየጠላ
ቂም ይዞ ሲጸልይ ሲዘምር አይፈራ
ይህ ልቤ ይቅርታን ማድረግ ካላወቀ
ከአንተ የሚያገኘው ምህረት አለቀ
አዝማች · Chorus
(ይሄውና ልቤ) ማይገባውን አስቀመጠና ይሄው ተበላሸ
(ይሄውና ልቤ) በሰው እያዘነ ውስጡን ውስጡን ግን ልቤ ቆሸሸ
(ይሄውና ልቤ) እስቲ ለውጠው ይህ ካልሆነ እጐዳለሁና
(ይሄውና ልቤ) ንጹህ ልብ ስጠኝ አንተን ለማየት አልችልምና
(ይሄውና ልቤ)
ቁጥር 4 · Verse 4
ወጣሁኝ ተሳካልኝ ሆነልኝ ብዬ
ሌት ተቀን ሳመሰግን በዝቶ ደስታዬ
የእኔን መውደቅና ሃዘን የሚመኝ
ይመጣል ከወጣሁበት ሊያወርደኝ
ይህ ልቤ አንተን አምኖ ካልጠነከረ
ይረታል መጨረሻው ያው ተሰበረ
አዝማች · Chorus
(ይሄውና ልቤ) የእኔን መሳካት መከናወኔን ክፉ ሲሰማ
(ይሄውና ልቤ) ብዙ ይተጋል ከአንተ ሊለየኝ ልቤን ሊያደማ
(ይሄውና ልቤ) ካልጠነከረ የአንተ ለመሆን ካላመረረ
(ይሄውና ልቤ) ቶሎ ይረታል በአንተ ፍቅር ካልተቃጠለ
(ይሄውና ልቤ)
ቁጥር 5 · Verse 5
አንዳንዴ ይሄ ልቤ ይጠራጠራል
ስትዘገይ የማትሰማውም ይመስለዋል
ነገሮች ብዙ በላዩ ሲከብዱበት
ሲያዝን የተናገርከው ሲጠፉበት
ለሚያልፍ ከእኔ ጋራ ለማይቆየዉ
ሲሸነፍ ይሄውልህ ጌታ እየዉ
አዝማች · Chorus
(ይሄውና ልቤ) በፍፁም ልብህ ታመን ያልከው እረሳሁና
(ይሄውና ልቤ) ተጠራጠረ የማያልፍ መስሎት ደነበረና
(ይሄውና ልቤ) ኧረ ፈውሰው ከሃሳብህ ጋር እስኪ አስማማው
(ይሄውና ልቤ) ይኸው ለውጠው ልብህን ክደህ ??? እጠበው
(ይሄውና ልቤ)
ቁጥር 6 · Verse 6
ልቤን ይኽው እያት ወደ አንተ መልሳት
ልቤን ይኸው እያት እንደ አንተ አድርጋት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ