እግዚአብሔር ይነሳል
Egziabhier Yenesal
2006 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር ይነሳል ክብሩን ይመልሳል
እኔ እምቢ ብል እንኳን ትውልድን ያስነሳል
ጌታዬ ይነሳል ክብሩን ይመልሳል
እኔ እምቢ እንኳን ያናውን ያስነሳል
ፍቅር ተለማምዶ ምህረት የሚያወራ
አንተን አሳዝኖ ምንም የማይፈራ
ሲታይ መልአክ ነው ውስጡ የፈረሰ
ሊታደስ ይችላል ሃይልህ ከፈሰሰ
አዝማች · Chorus
አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን
እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን
ቁጥር 2 · Verse 2
አንዱ ከአንዱ ጋራ የታለ ፍቅር
መያያዙን ትቶ ወሬ ሲቆፍር
አንድነት የለውም ተነካክሶ አለቀ
ይሄ ክፉ መዘዝ ለሌላም ዘለቀ
አዝማች · Chorus
አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን
እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን
ቁጥር 3 · Verse 3
መለክት አለኝ ብሎ ከቃልህ የወጣ
ከአንተ አስመስሎ ከራሱ ያመጣ
በስሜት ተገፍቶ ህዝቡን እያመሰ
በዚህ ነገር እንኳን ስንቱ አለቀሰ
አዝማች · Chorus
አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን
እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን
ቁጥር 4 · Verse 4
በዕውቀት ተወጥሮ መስሎት የአደገ
ለስተቱ ሁሉ ጥቅስ እየፈለገ
ያለ እየመሰለው ጠፋ ይሄ ስዉ
ማወቅ መች ጠቀመው ሕይወት ከሌለው
አዝማች · Chorus
አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን
እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን
ቁጥር 5 · Verse 5
እግዚአብሔር ይነሳል ክብሩን ይመልሳል
እኔ እምቢ ብል እንኳን ትውልድን ያስነሳል
ይሄ ለጥቅሙ ያኛውን ሲገፋ
ራሱን ለማሳየት መለከት ሲያስነፋ
የአንተን ተወት አድርጐ ለእራሱ ሲጥር
ክብርህን ተጋፍተውን ጠፍተን እንዳንቀር
ሕይወትን ሰጥተኸው ከእጅህ ላይ በልቶ
እንዴት ነው ሚለየው ሄዶ ተቀይጦ
ስምህን ግን ይዟል ተግባሩ ግን ሌላ
እየተዘናጋን ጽዋህ እንዳትሞላ
አዝማች · Chorus
አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን
እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን
ቁጥር 6 · Verse 6
እስቲ ጠብቀን ትንሽ ታገሰን
እንመለሳለን ሳታዋርደን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ