ባለውለታዬ
Balewuletayie
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እወድሃለሁ ጌታ አድነኸኛል
አመልክሃለሁ ኢየሱስ ቤዛ ሆነኸኛል
አመሰግናለሁ ጌታ ታድገኸኛል
አከብርሃለሁ ኢየሱስ ልጅ አድርገኸኛል
ላመስግንህ ጠዋትና ማታ
ከዚህ በላይ ይገባሃል ጌታ
ላመስግንህ ጠዋትና ማታ
ይሄ ብቻ አይበቃህም ጌታ
ከሞት መንደር በምህረትህ በቸርነትህ አውጥተህ
ጨለማውን አስወግደህ ለዚህ ክብር ያበቃኸኝ
ሳትሰለች እያባበልክ ኃጢአት በደሌን ታግሰህ
ሰው አረግከኝ አተረፍከኝ ነፍሴን ከጥፋት መልሰህ
አዝማች · Chorus
ባለውለታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ
ባለውለታዬ ጌታዬ ዋሴ ጠበቃዬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያለ እረኛ ስቅበዘበዝ በዓለም ወጥመድ ተይዤ
ፈጣሪዬን ስበድል ሳሳዝን በክፉ ደንዝዤ
እራራህልኝ ደረስክልኝ ጸያፍ ታሪኬን ቀየርከው
ልጅ ተባልኩኝ ክብር አገኘሁ ስሜን በደም ቀለም ጻፍከው
አዝማች · Chorus
ባለውለታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ
ባለውለታዬ ጌታዬ ዋሴ ጠበቃዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ