ባለውለታዬ
አማርኛ
አዝማች · Chorus
ስራዬን ሰርተህልኛል እዳዬን ከፍለህልኛል
መንገዴ ተቃንቶልኛል አንተን ማየት ሆኖልኛል
በዘለዓለም ፍቅርህ ወድደኸኛልና
ምሥጋና አይጠፋም ከአፌ ምሥጋና (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተ የደስታዬ ምንጭ ውዴ የሰላሜ ንጉሥ
ከትቢያ ላይ ያነሳኸኝ ክበር ተመስገን ኢየሱስ
ባለፍኩበት መንገድ ሁሉ አይቻለሁ ማዳንህን
ሳልታክት አወራዋለሁ አምላኬ ሕያው ስራህን
በተከበበ ከተማ ምህረትህ በዝቶልኝ
በድል መንገድ እየመራህ ከጠላቴ አስጥለኀኝ
የሞተውን ማንነቴን ሕይወት ዘርተህበታል
ከብረህልኛል በቤቴ በረከትህ በርክቷል (፪x)
አዝማች · Chorus
ስራዬን ሰርተህልኛል እዳዬን ከፍለህልኛል
መንገዴ ተቃንቶልኛል አንተን ማየት ሆኖልኛል
በዘለዓለም ፍቅርህ ወድደኸኛልና
ምሥጋና አይጠፋም ከአፌ ምሥጋና (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የዓለም እንከን የሞላበት ውል አልባ ሆኖ መንገዴ
አንተን እንዳላይ ከልሎኝ አጉል ወግና ልማዴ
ምንም በጐነት ሳይኖረኝ እንዲያው ምህረት አግኝቼ
የደምህ ፍሬ ሆኛለሁ ከኀጢአት ባሕር ወጥቼ
ምሥጋናዬን ልሰዋልህ ክበርልኝ ዘለዓለም
በዘመኔ ሁሉ ለእኔ እንዳንተ መልካም የለም
እፎይ ብያለሁ አርፌ ሆነኸኛል ሰላሜ
ተባረክልኝ ልበልህ ደግሜ ደጋግሜ (፪x)
አዝማች · Chorus
በዘለዓለም ፍቅርህ ወድደኸኛልና
ምሥጋና አይጠፋም ከአፌ ምሥጋና (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሞተውን ማንነት ሕይወትን ዘርተህበት
ጽድቅህን ሰጥተኸኝ ለእኔ ነፃ አረግከኝ ከኩነኔ
አዝማች · Chorus
በዘለዓለም ፍቅርህ ወድደኸኛልና
ምሥጋና አይጠፋም ከአፌ ምሥጋና (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ