አልመለስም
Alemelesem
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የከበረውን ከተዋረደው ለይቼ
ዐይኔ ተገልጦልኝ አምላኬ ያየልኝን አይቼ
ለሕያው ተስፋ ተለይቼያለሁ ወስኜ
ንቄ ትቼዋለሁ ዓለማዊነትን ጨቅኜ
በእውነት ተረትቻለሁ በእውነት
ለሕይወት ተጠርቻለሁ ለሕይወት
በፍቅር ተሸንፌአለሁ በፍቅር
ለክብር ተለይቻለሁ ለክብር
(እህም) መጐናጸፊያ ወድቆብኝ (እህ) እንድከተለው ጌታዬን
(እህም) ሞፈር ቀንበሬን ሰብሬ (እህ) ጨክኜ ትቼው እርሻዬን
(እህም) ምን ቀረኝ ብዬ ልመለስ (እህ) የያዝኩት ከእንቁ ይበልጣል
(እህም) ሰው ክርስቶስ ተገልጦለት (እህ) ዓለምን እንዴት ይመርጣል
አዝማች · Chorus
አልመለስም ወደኋላ አልመለስም (አልመለስም) (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሆድ ሳልረሳ ከጥንቱ ያወቀኝ
በእናቴ ማህጸን ሳለሁ የቀደሰኝ
በአስደናቂ ፍቅሩ ልቤን አሸንፎ
ተክሎኛል በቤቱ በምክሩ ደግፎ
የዘለዓለሙን ተስፋ ጸንቶ የሚኖረውን
በእጅ ያልተዳሰሰ የሰው ዐይን ያላየው
ዋናዬን አግኝቻለሁ ከቶ አልመኝም ሌላ
ዓለምና ምኞቱን አላይም ወደኋላ
አዝማች · Chorus
አልመለስም ወደኋላ አልመለስም (አልመለስም) (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የከበረውን ከተዋረደው ለይቼ
ዐይኔ ተገልጦልኝ አምላኬ ያየልኝን አይቼ
ለሕያው ተስፋ ተለይቼያለሁ ወስኜ
ንቄ ትቼዋለሁ ዓለማዊነትን ጨቅኜ
በእውነት ተረትቻለሁ በእውነት
ለሕይወት ተጠርቻለሁ ለሕይወት
በፍቅር ተሸንፌአለሁ በፍቅር
ለክብር ተለይቻለሁ ለክብር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ