ቃል ነው መሠረቴ
Qal New Meseretie
አማርኛ
አዝማች · Chorus
በጐርፍ በነፋስ አይወሰድም ቤቴ
አስተማማኝ አለት ቃል ነው መሠረቴ (፪x)
ቃል ነው መሠረቴ ቃል ነው (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በእርሱ የታመነ ቤቱ አለት ላይ ነው
ነፋሱም አይገፋው ወጀብ አይጥለው
ሕያው የሚሰራ ቃል አለኝና
አሻግሬ የማየው ድል አለ ገና
አነስተኛ ቢመስልም ጅማሬዬ
እጅግ ታላቅ ይሆናል ፍጻሜዬ
ትምክህቴ ከላይ ነው ከአርያም
ነገ ምን ይሆናል ብዬ አልሰጋም
ሳልናወጥ መቆሜ ፍጥረት ሁሉ ደንቆታል
የአምላኬ ሰላም ወርዶ ልቤን ሙሉ አድርጐታል
አወዳደቁ ታላቅ መጨረሻው የከፋ
እንደ አሸዋ ላይ ቤት አይደለም የኔ ተስፋ
መኖሪያዬ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ለዘለዓለም (፬x)
ፀጋ ወርዶልኛል ከአርያም በፍፁም ወደኋላ አልልም
ለሰማዩ ርስቴ እጋደላለሁ በአምላኬ ታምኜ እወርሰዋለሁ
የሚያስጨንቀኝን በእርሱ ላይ ጥዬ በወደደኝ ጌታ ተደላልድዬ
እተማመናለሁ በቃልኪዳኑ አይርድም ጉልበቴ ቢከፋም ቀኑ
አዝማች · Chorus
በጐርፍ በነፋስ አይወሰድም ቤቴ
አስተማማኝ አለት ቃል ነው መሠረቴ (፪x)
ቃል ነው መሠረቴ ቃል ነው (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከመቅደሱ የወጣ የወረደ ከሰማይ
እርሱ ነው መመኪያዬ የማዕዘኑ ድንጋይ
በእምነት የታነጸ ጥብቅ ነው መሠረቴ
በሽብር አይናጋ አይናወጥም ቤቴ
መኖሪያዬ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ለዘለዓለም (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ