Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፀጋህ ያግዘኝ

Tsegah Yagzegn

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፀጋህ ያግዘኝ እንጂ

መንፈስህ ይምራኝ እንጂ

ምን አቅም አለኝ እኔ

በአንተው ነው ሰው መሆኔ (፪x)

ጌታዬ ጌታዬ ጌታዬ

አንተ ነህ ለእኔ ዋስትናዬ (፪x)

የዘለዓለም እቅድህን በእኔ ያለህን አላማ

ፈጽሜ ደስ እንዳሰኝህ እርዳኝ ከሐሳብህ ልስማማ

በሚሰማ በሚታየው እንዳልወሰድ ከቤትህ

ምራኝ እጆቼን ያዝና ሁልጊዜ ልኑር በፊትህ (፪x)

እርዳኝ እንዳላሳዝንህ እርዳኝ (፫x)

እርዳኝ በቤትህ እንድኖር እርዳኝ

ፀጋህ ያግዘኝ እንጂ

መንፈስህ ይምራኝ እንጂ

ምን አቅም አለኝ እኔ

በአንተ ነው ሰው መሆኔ (፪x)

ጌታዬ ጌታዬ ጌታዬ (ጌታዬ)

አንተ ነህ ለእኔ ዋስትናዬ (ዋስትናዬ) (፪x)

እምነት እንደጐደለው ሰው መጠራቴ እንዳይቀርብኝ

የፈቃድህን ምሥጢር እንዳውቅ ጥበብ ማስተዋልን ስጠኝ

ስንፍናዬ ከኔ ርቆ እንዲያምር መጨረሻዬ

መልካም ፍሬ እንዲገኝብኝ ደግፈኝ ከመነሻዬ (፪x)

እርዳኝ (እርዳኝ) እንዳላሳዝንህ እርዳኝ (፫x)

እርዳኝ (እርዳኝ) በቤትህ እንድኖር እርዳኝ

ፀጋህ ያግዘኝ እንጂ

መንፈስህ ይምራኝ እንጂ

ምን አቅም አለኝ እኔ

በአንተ ነው ሰው መሆኔ (፪x)

ጌታዬ ጌታዬ ጌታዬ (ጌታዬ)

አንተ ነህ ለእኔ ዋስትናዬ (ዋስትናዬ) (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ