Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ገለል ይላል

Gelel Yelal

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እኔ ግን ሁሉን ለሚችለው ለርሱ ተለይቻለሁ

በተቀደሰው ተራራዬ ንጉሤን ሾሜዋለሁ (፪x)

አመልከዋለሁ በቤቴ አከብረዋለሁ

አነግሰዋለሁ በልቤ እቀድሰዋለሁ (፪x)

ከተነገረለት ከተባለው በላይ

ትልቅ ነው አምላኬ በምድር በሰማይ

እሰግድለታለሁ ይገባዋል እሱ

ከፍ አደርገዋለሁ በቤተ መቅደሱ

ኤልሻዳዩን አምላክ ሳመልከው ከልቤ (፪x)

ስሙን ሳወድሰው በፍፁም ሃሳቤ (፪x)

ምን ይሳነዋል ጌታ ታምራት ይሆናል (፪x)

የሚገዳደረኝም ጥሎኝ ገለል ይላል

ገለል ይላል (፫x)

ከፊቴ ገለል ይላል (፪x)

ቢመከር ቢዶለት ወጥመድ ቢዘረጋ

የጠላት ሠራዊት ሺህ ሆኖ ቢንጋጋ

እውነት እንደ ጋሻ ዙሪያዬን ከብቦኝ

ምልክት አለብኝ በየት ሊያገኘኝ

በነፍሥም እንኳን ቢሆንም እወራረዳለሁ (፪x)

ከሚነድም እሳት ያድናል አምናለሁ (፪x)

የቃልኪዳን ልጅ ነኝ ይሄው ነው ትምክህቴ ጌታ ነው ትምክህቴ

ጭንገፋና እርግማን አይገቡም በቤቴ (፪x)

የጌታን ሥም ስጠራ ችግር ቢሆን መከራ

ኢየሱስን ስጠራ ሸለቆ ቢሆን ተራራ

የስልጣኑን ጉልበት መቼ ይቋቋማል

ገለል ይላል ከፊቴ ገለል ይላል (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ