Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቸር ነውና

Cher Newena

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቸር ነውና ምህረቱ የለው ወደር

ክብር ይሁንለት በሰማይ በምድር

እልል በሉ ዘምሩለት በበገና

አምልኮ ለእግዚአብሔር ይገባዋልና

ይገባዋል (፰x)

ሰማይና ምድርን በቃሉ ያጸና

ሁሉን የፈጠረ ኃያል ባለዝና

በእውነት እንደ ቃሉ ፍፁም የታመነ

አልፋና ኦሜጋ ኤልሻዳይ የሆነ

ዘለዓለማዊ አምላክ ሁሉ ይቻለዋል

አምልኮና ስግደት ክብር ይገባዋል

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፬x)

ቸር ነውና ምህረቱ የለው ወደር

ክብር ይሁንለት በሰማይ በምድር

እልል በሉ ዘምሩለት በበገና

አምልኮ ለእግዚአብሔር ይገባዋልና

ይገባዋል (፰x)

የሞት አዋጅ ሽሮ ሕይወትን የሚሰጥ

መራራውን ሃዘን በሳቅ የሚለውጥ

አጥፊውን አጥፍቶ ምስኪኑን ያከብራል

ሃሳቡ እንደዋዛ መቼ ይከለከላል

ማደሪያው ይባረክ ክብር ይሁንለት

የፍጥረታት ጌታ የሕያዋን አባት

ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ