በከፍታ
Bekefta
ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የምትሰራውን ስለምትመዝን
በሚሆነው ነገር እኔ አላዝን
የማመልክህ አምላክ ለኔ ልዩ ነህ
ለተገፉት ደራሽ በጸድቅ ትፈርዳለህ
አዝማች · Chorus
በከፍታ በዝቅታ በሃዘንም በደስታ
አንተን አከብራለሁ ጌታን አንተን አከብራለሁ
አንተን አከብራለሁ ኢየሱስ አንተን አከብራለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ለኔም ምታስበው በጐና መልካም ነው
ክፉ ሃሳብ አይደል የሰላም ሃሳብ ነው
ከኔ የበለጠ ለኔ ታስባለህ
ከእናት ከአባት ይልቅ ትጠነቀቃለህ
አዝማች · Chorus
በከፍታ በዝቅታ በሃዘንም በደስታ
አንተን አከብራለሁ ጌታን አንተን አከብራለሁ
አንተን አከብራለሁ ኢየሱስ አንተን አከብራለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
በወይንም ሐረግ ውስጥ ፍሬ ባይገኝ
ትናንት የነበረኝ ዛሬ ባይኖረኝ
ማታ ባለቅስ እንኳን ጠዋት እስቃለህ
ስለዚህ ሁልጊዜ አንተን አከብራለሁ
አዝማች · Chorus
በከፍታ በዝቅታ በሃዘንም በደስታ
አንተን አከብራለሁ ጌታን አንተን አከብራለሁ
አንተን አከብራለሁ ኢየሱስ አንተን አከብራለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሰማዩ ቢጠራ ደመናም ባይኖርም
ምልክት ባይታይ ነፋስም ባይነፍስም
በገናዬን ይዤ እደረድራለሁ
ሸለቆ ሲሞላ በዓይኔ አየዋለሁ
አዝማች · Chorus
በከፍታ በዝቅታ በሃዘንም በደስታ
አንተን አከብራለሁ ጌታን አንተን አከብራለሁ
አንተን አከብራለሁ ኢየሱስ አንተን አከብራለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ