የከንቱ ከንቱ ነው
Yekentu Kentu New
ትራክ 11 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አይን ከማየት አይጠግብም
ጆሮም ከመስማት አይሞላም
በአለም ያለው ከንቱ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
የከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው ንፋስን እንደመከተል ነው (፪x)
እግዚአብሄር ሆይ በዘመኔ ይህን እሻለሁ
ክብርህን ሳይ ብቻ እጠግባለሁ (፪x)
አምላኬ ሆይ በዘመኔ ይህ እሻለሁ
ክብርህን ሳይ ብቻ እጠግባለሁ (፪x)
ሁሉን አየሁ ተመለከትኩ
ከአንተ ሌላ እርካታ እንደሌለ አወቅኩ
ሁሉም ከንቱ እጅግ ከንቱ ነው
አንተን ማግኘት ጌታ የጥበብ ጥበብ ነው
አዝማች · Chorus
አይን ከማየት አይጠግብም
ጆሮም ከመስማት አይሞላም
በአለም ያለው ከንቱ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
የከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው ንፋስን እንደመከተል ነው (፪x)
እግዚአብሄር ሆይ በዘመኔ ይህን እሻለሁ
ክብርህን ሳይ ብቻ እጠግባለሁ (፪x)
አምላኬ ሆይ በዘመኔ ይህ እሻለሁ
ክብርህን ሳይ ብቻ እጠግባለሁ (፪x)
ሃብትም ንብረት አላፊ ነው
ውበትም ደም ግባት ቁንጅና ጠፊ ነው
ከሁሉም በላይ የምታስመካ
አንተ ነህ ጌታ ሆይ የዘላለም ተስፋ
አዝማች · Chorus
አይን ከማየት አይጠግብም
ጆሮም ከመስማት አይሞላም
በአለም ያለው ከንቱ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
የከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው ንፋስን እንደመከተል ነው (፪x)
እግዚአብሄር ሆይ በዘመኔ ይህን እሻለሁ
ክብርህን ሳይ ብቻ እጠግባለሁ (፪x)
አምላኬ ሆይ በዘመኔ ይህ እሻለሁ
ክብርህን ሳይ ብቻ እጠግባለሁ (፪x)
ትውልድ ሄዶ ትውልድ ይመጣል
ጸንቶ ሚኖር የለም ሁሉም ይለወጣል
የማይለወጥ ፍጹም የሆነ
አምላኬ ብቻ ነው ሁሌ የታመነ
አዝማች · Chorus
አይን ከማየት አይጠግብም
ጆሮም ከመስማት አይሞላም
በአለም ያለው ከንቱ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
የከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው
ንፋስን እንደመከተል ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ