ክበር ትልሃለች
Keber Telehalech
ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አዳኝ ነህ ከእስራት ምትፈታ
ለጠላጥህ የማትረታ
የኔን ነፍስ ከጠላት ተሟግተህ
አዳንካት ከእስራቷ ፈተህ
አዝማች · Chorus
ያዳንካትም ነፍሴ ሁልጊዜ ሁሌ ሁልጊዜ
ክበር ትልሃለች ጌታ እየሱሴ (፪x)
ክበር ክበርልኝ ጌታዬ ክበር ክበርልኝ
ንገሥ ንገሥልኝ ጌታዬ ንገሥ ንገሥልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከነኃጥያቴ ያኔ ወደድከኝ
ዘላለም ያንተው አደረከኝ
ጌታ ሆይ በእውነት ፍቅር ነህ
እኔን የሚወድድ ልብ አለህ
አዝማች · Chorus
ያዳንካትም ነፍሴ ሁልጊዜ ሁሌ ሁልጊዜ
ክበር ትልሃለች ጌታ እየሱሴ (፪x)
ክበር ክበርልኝ ጌታዬ ክበር ክበርልኝ
ንገሥ ንገሥልኝ ጌታዬ ንገሥ ንገሥልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
የኔ ሩጫ ውጊያው ከንቱ ነው
ሰልፉ የአንተ ነው አምናለሁ
ቆሜ ማዳንህን እያየሁ
ለነገም ተስፋ አደርግሃለሁ
አዝማች · Chorus
ያዳንካትም ነፍሴ ሁልጊዜ ሁሌ ሁልጊዜ
ክበር ትልሃለች ጌታ እየሱሴ (፪x)
ክበር ክበርልኝ ጌታዬ ክበር ክበርልኝ
ንገሥ ንገሥልኝ ጌታዬ ንገሥ ንገሥልኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ማዳኑ ለሚፈሩት ቅርብ ነው
ምህረቱ እስከልጅ ልጆች ነው
እኔም ሳላቋርጥ እጠራሃለሁ
ክብርህንም እንዳይ አምናለሁ
አዝማች · Chorus
ያዳንካትም ነፍሴ ሁልጊዜ ሁሌ ሁልጊዜ
ክበር ትልሃለች ጌታ እየሱሴ (፪x)
ክበር ክበርልኝ ጌታዬ ክበር ክበርልኝ
ንገሥ ንገሥልኝ ጌታዬ ንገሥ ንገሥልኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
ከልብ የማይጠፋ ዉለታ አለብኝ
ጌታዬ ለኔ ያደረገልኝ
በእድሜ ዘመን ሁሉ እገዛለታለሁ
በቤቱም ሁሌ አዘማለሁ
ተመስገን እለዋለሁ
ከእግሩ ስር አሰግዳለሁ (፪x)
ምስጋናዬ ይብዛልህ ክበርልኝ
ዛሬም አይነስብህ ይድረስልህ (ሃሌሉያ)
አምላኬ ሆይ ለአንተ የምሰጠው
ጠዋት ማታ ወዳንተ ማሳርገው
ክበር ክበርልኝ ጌታዬ ክበር ክበርልኝ
ንገሥ ንገሥልኝ ጌታዬ ንገሥ ንገሥልኝ
በስራህ ነው ጌታ በስራህ
በአዲስ ዝማሬ በአፌ የጨመርህ
ልቤን በደስታ ስለሞላኸው
ሁሌ ለአንተ እንድዘምር ነው
ተመስገን እልሃለሁ
ከእግሩ ስር አሰግዳለሁ (፪x)
ምስጋናዬ ይብዛልህ ክበርልኝ
ዛሬም አይነስብህ ይድረስልህ (ሃሌሉያ)
አምላኬ ሆይ ለአንተ የምሰጠው
ጠዋት ማታ ወዳንተ ማሳርገው
ክበር ክበርልኝ ጌታዬ ክበር ክበርልኝ
ንገሥ ንገሥልኝ ጌታዬ ንገሥ ንገሥልኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ