Bethlehem Wolde/Cher Neh/Balewuletayie
ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ባለውለታዬ ጌታዬ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ
ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ውለታህን አስታውሰዋለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ለኔ ነው መንከራተትህ
መስቀል ተሸክመህ መውረድህ
ለኔ የደም ላብ ያላበህ
ፍቅር ነው እንዲህ ያስጨነቀህ
አዝማች · Chorus
ውለታህን አስታውሳለሁ
ፈቅጄም አመልክሃለሁ
ውለታህን አስታውሳለሁ
ወድጄም አመልክሃለሁ
ባለውለታዬ ጌታዬ ...
ቁጥር 4 · Verse 4
ከአብ ዘንድ ለኔ የተሰጠ
ትልቁ ስጦታዬ አንተ ነህ
ይህ ሚስጥር ለኔ ተገልጾል
መዳን ከአንተ ዘንድ ሆኖልኛል
አዝማች · Chorus
ውለታህን አስታውሳለሁ
ፈቅጄም አመልክሃለሁ
ውለታህን አስታውሳለሁ
ወድጄም አመልክሃለሁ
ባለውለታዬ ጌታዬ ...
ቁጥር 5 · Verse 5
ልከፍለው እማልችል ውለታ
ያኔ ያረከውን በጐልጐታ
ምስጋናን ሙገሳን ይዤ
ላክብርህ ኢየሱስ ወዳጄ
አዝማች · Chorus
ውለታህን አስታውሳለሁ
ፈቅጄም አመልክሃለሁ
ውለታህን አስታውሳለሁ
ወድጄም አመልክሃለሁ
ባለውለታዬ ጌታዬ ...
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ