ግዛኝ
Gezagn
ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔስ እግዚአብሄር ሆይ በአንተ እምካለሁ
በክንፎችህ ጥላ ሁልጊዜ አርፋለሁ
በኔ ላይ የተሾምክ አንተ ብቻ ጌታ
እገዛልሃለሁ ዛሬም በደስታ፣ዛሬም በደስታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ግዛኝ አንተ ብቻ ፣ ግዛኝ እገዛለሁ
ግዛኝ በሕይወቴ ላይ ፣ ግዛኝ ሾሜሃለሁ
ግዛኝ አንተ ብቻ ፣ግ ዛኝ እገዛለሁ
ግዛኝ በልቤ ላይ ፣ ግዛኝ ሾሜሃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
አስፈራርተህ አይደል እኔን የጠራኀኝ
በቀራንዮ ፍቅርህ ስበህ እየማረከኝ
እስከሽምግልና ልትሸከመኝ
የወደድከኝ ጌታ ለዘላለም ግዛኝ ፣ ለዘላለም ግዛኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ግዛኝ አንተ ብቻ ፣ ግዛኝ እገዛለሁ
ግዛኝ በሕይወቴ ላይ ፣ ግዛኝ ሾሜሃለሁ
ግዛኝ አንተ ብቻ ፣ግ ዛኝ እገዛለሁ
ግዛኝ በልቤ ላይ ፣ ግዛኝ ሾሜሃለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ወደኸኛል ጌታ እኔም ወድጄሃለሁ
የዘላለም ምርጫ አንተን አድርጌያለሁ
የአንተ በመሆኔ በጣም ረክቻለሁ
እጆቼን አንስቼ ግዛኝ እልሃለሁ ፣ ግዛኝ እልሃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ግዛኝ አንተ ብቻ ፣ ግዛኝ እገዛለሁ
ግዛኝ በሕይወቴ ላይ ፣ ግዛኝ ሾሜሃለሁ
ግዛኝ አንተ ብቻ ፣ግ ዛኝ እገዛለሁ
ግዛኝ በልቤ ላይ ፣ ግዛኝ ሾሜሃለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ