ታምራትን
Tameraten
ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ብቻህን ታምራትን አንተ ትሰራለህ
የማመልክህ እግዚአብሄር አንተ ሁሉንም ቻይ ነህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ደመና ሳታሳይ ዝናብ ታዘንባለህ
ከደረቀው አለት ውሃ ታፈልቃለህ
በቃልህ ስታዝዘው ሁሉ ይታዘዝሃል
የፍጥረት ገዢ ነህ ማንስ ይመስልሃል
ብቻህን ታምራትን አንተ ትሰራለህ
የማመልክህ እግዚአብሄር አንተ ሁሉንም ቻይ ነህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ኢየሱስ ለኔ እጅግ ልዩ ነህ
ለሰው ሁሉ ወዳጅ ሁሉ የተቻለህ
እኔም ባንተ ጌታ እተማመናለሁ
ሞትንም ወስደሃል እኮራብሃለሁ
ብቻህን ታምራትን አንተ ትሰራለህ
የማመልክህ እግዚአብሄር አንተ ሁሉንም ቻይ ነህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ማንም ሳያቅትህ ማንም ሳይመክርህ
ዓለምን ሞላዋን አንተ መሠረት
ወብና ድንቅ አርገህ እኛን ፈጥረኸናል
የእጆችህ ስራዎች አመስግነንሃል
በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ
ጌታ መልካም ነው ይሰጣል እረፍት
እርሱን ታምኖ ጠብቆ ያፈረ ማነው
ጸሎቴን ሰምቷል ጌታን ላክብረው
አዝማች · Chorus
ዛሬም ላሞጋግስህ ክበርልኝ ክበርልኝ
ውለታህን ልቁጠረው ንገሥልኝ ንገሥልኝ
ጸሎቴን ሰምተሃል ክበርልኝ ክበርልኝ
ጠላቴን ረግጠሃል ንገሥልኝ ንገሥልኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
ከፍ በል ዝማሬ ይድረስህ
ሌላማ የለኝም የምሰጥህ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ጌታን የሚጠብቁ ቅዱሳን ሁሉ
ከመልካም ነገር አንዳች አይጐድሉ
እኔም በዘመኔ ተጠግቼዋለሁ
ከመልካም ነገር ሁሌ እጠግባለሁ
አዝማች · Chorus
ዛሬም ላሞጋግስህ ክበርልኝ ክበርልኝ
ውለታህን ልቁጠረው ንገሥልኝ ንገሥልኝ
ጸሎቴን ሰምተሃል ክበርልኝ ክበርልኝ
ጠላቴን ረግጠሃል ንገሥልኝ ንገሥልኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ