በርታ
Berta
2017 · ትራክ 13 · 5:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሕይወት ጉዞ ላይ
ቢያደከም መንገዱ
የፈተናው ብዛት ዉጣ ውረዱ
ግን የያዝከው ተስፋ
ከአምላህ ከጌታ
ቁጥር 2 · Verse 2
የጰና ነውና ወገኔ በርታ (2x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምናልባትም በጊዜያዊ ፈተና ተጨቀሃል
በብዙማ በብዙ ሃዘን በቅሶ ውስጥ አልፈሃል
ግን ያሁኑ የሚያበቃ የሚያከትም የሚያልፍ ነውና
ለዘላለም የፅና የሕይወት ቃል አለህና
አይዞህ በርታ ጭክን በል በእምነት ፅና
አዝማች · Chorus
እመጣለሁ ያለህ ጌታ ይመጣልና(2x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በምድር ላይ የሰው ሕይወት ሰልፍ ነው የጦር ሜዳ
ሕይወት ሩጫ ለማዘግየት የሚጥር የሚጐዳ
ጦርነቱን ለማሸነፍ ብትፈልግ ልትረታ
አስተውለው የሰጠህን ክቡር ቃል የአንተ ጌታ
አይዞህ በርታ ጭክን በል በእምነት ፅና
አዝማች · Chorus
እመጣለሁ ያለህ ጌታ ይመጣልና(2x)
ቁጥር 5 · Verse 5
አለኝ ያልከው በጅህ ያለው ተበትኖ ቢጠፋ
ግራ ቀኙ ቢዘጋብህ ብታጣ የሚሆን ተስፋ
ሰማያትን ምድርን የሰራው ጌታ ረዳትህ
ብሰማው ብትፈቅድ ለአፍታ ጊዜ ሰተህ
አይዞህ በርታ ጭክን በል በእምነት ፅና
አዝማች · Chorus
እመጣለሁ ያለህ ጌታ ይመጣልና(2x)
ቁጥር 6 · Verse 6
በሕይወት ጉዞ ላይ
ቢያደከም መንገዱ
የፈተናው ብዛት ዉጣ ውረዱ
ግን የያዝከው ተስፋ
ከአምላህ ከጌታ
የፀና ነውና ወገኔ በርታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ